ዓመታዊ ቁጠባ ከሁለት ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል
የኢትዮጵያ ባንኮች ያስከፈቱት አካውንት ብዛት 129 ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች ያላቸውን ቅርንጫፍ ብዛት ከ11 ሺህ በላይ ደርሷል ብሏል።
የሀገሪቱ አጠቃላይ ባንኮችም 129 ሚሊዮን አካውንት ማስከፈታቸውን ባንኩ ገልጿል።
ባንኮቹ በየቅርንጫፎቻቸው ከቆጣቢዎች የሰበሰቡት ገንዘብ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ሲደርስ በብድር መልክ ደግሞ ሁለት ትሪሊዮን ብር ሰጥተዋል ተብሏል።