ፕሬዝዳንቱ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የጀመረችውን ጦርነት ብታቆም በሀገርነት አትቀጥልም ብለዋል
ቀጣዩ ጊዜ ለዩክሬን ከባድ እንደሚሆን የሰሜን አትለንጊክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ)ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር የጀመረችው ጦርነት 100ኛ ቀኑ ላይ ይገኛል።
ጦርነቱን ሁለቱ ሀገራት በቀጥታ ይዋጉ እንጂ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ከጀርባ ሆነው ዩክሬንን በመርዳት ላይ ናቸው።
የቀድሞው የስዊድን ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የኔቶ ፕሬዝዳንት ጀንስ ስቶልትንበርግ ከፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንዳሉት ሩሲያ ጦርነቱን ካቆመች ጥሩ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ይሁንና ሩሲያ ጦርነቱን ካላቆመች እና ዩክሬን መከላከሏን ከቀጠለች ቀጣዩ ጊዜ ለኬቭ ከባድ ይሆናል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት ጦርነቱን ለማስቆም ድርድር ማድረጋቸው ዋነኛው መፍትሄ ይሆናል የሚሉት ስቶልትንበርግ፣ ዩክሬን በዚህ ጦርነት ከተሸነፈች እንደ ሀገር አትቀጥልም ሲሉ አሳስበዋል።
በተለይም ጦርነቱ ከቀጠለ ቀጣዩ የቅዝቃዜ ወራት ለዩክሬን ዋና ፈተና እንደሚሆን የተናገሩት የኔቶ ፕሬዝዳንት ለዩክሬናዊያን ወታደሮች የቅዝቃዜ ወቅቶች አልባሳት እና የጦር መሳሪያ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።
የሩሲያ ነዳጅ ወደ አውሮፓ አለመግባቱን ተከትሎ በአውሮፓዊያን ዜጎች ላይ በተከሰተው የኑሮ ውድነት መሰላቸት እየታየ ነው፣ ይሁንና ዩክሬናዊያን ግን ህይወታቸውን እያጡ ነው ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።
ዩክሬን 20 በመቶ የሚሆነው ግዛቷ በሩሲያ ጦር የተወሰደባት ሲሆን አሜሪካ ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ አግኝታለች።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።
ሩሲያ በበኩሏ ወደ ግዛቷ የሚገቡ ዩክሬናዊያን የሩሲያ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው እና ወርሀዊ ደመወዝ በመስጠት ላይ ትገኛለች።