በግለሰብ ደረጃ በቀን ከአንድ ባንክ ሊወጣ የሚችለው የብር መጠን ወደ 50 ሺ ዝቅ ተደረገ
ብሄራዊ ባንክ ከአሁን ቀደም ባወጣው የገንዘብ አወጣጥ መመሪያ ላይ ማሻሻያ አደርጓል
ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ተቋማት በቀን እስከ 75 ሺ ብር ለማውጣት ይችላሉም ተብሏል
በግለሰብ ደረጃ በቀን ከአንድ ባንክ ሊወጣ የሚችለው የብር መጠን ወደ 50 ሺ ዝቅ ተደረገ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በቀን ከባንክ ሊወጣ በሚችለው የብር መጠን ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
ማሻሻያው ባንኩ ከአሁን ቀደም በቁጥር FIS/03/2020 አውጥቶት በነበረው መመሪያ ላይ የተደረገ ነው፡፡
በተመለከተ ከአሁን ቀደም ባወጣው የገንዘብ አወጣጥ መመሪያ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
በባንኩ ምክትል ገዢ ሰለሞን ደስታ ተፈርሞ ትናንት ለሁሉም ባንኮች እና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የተላከው ደብዳቤ በመመሪያው ሁለት ንዑስ አንቀጾች ላይ በብር ለውጡ የታለሙ ግቦችን ለማሳካት በማሰብ ማሻሻያ መደረጉን ይጠቅሳል፡፡
ማሻሻያው በንዑስ አንቀጾቹ በሰፈረው እና በቀን ከፋይናንስ ተቋማቱ ሊወጣ በሚችለው ዕለታዊ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ላይ ለውጥ መደረጉን የሚጠቁም ነው፡፡
ስለሆነም በግለሰብ ደረጃ በቀን ከባንክ ሊወጣ የሚችለው ከፍተኛ የብር መጠን 50 ሺ፤ ህጋዊ ሰውነት ባላቸው ተቋማት ደረጃ ደግሞ 75 ሺ ነው፡፡
ብሄራዊ ባንክ ከባንክ ውጭ ያለውን የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ለመቆጣጠር በሚል የተለያዩ አዳዲስ መመሪያዎችን ባሳለፍነው ዓመት አውጥቶ ተግባር ላይ አውሏል፡፡
ባሳለፍነው ወርሃ ግንቦት አውጥቶት በነበረውና አሁን ባሻሻለው አዲስ መመሪያ በግለሰብ ደረጃ በቀን እስከ 2 መቶ ሺ በወር እስከ አንድ ሚሊዬን፤ በተቋም ደረጃ ደግሞ በቀን 3 መቶ ሺ በወር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዬን የሚደርስ ጥሬ ገንዘብ ከባንኮች እንዲወጣ ፈቅዶ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡