በአፍጋኒስታን ጦርነት ወደ 33ሺ የሚጠጉ ሕፃናት ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳተኛ ሆነዋል
በአሸባሪነት ተፈረጆ የነበረው ታሊባን ከ20 አመታት በኋላ ቤጸ ምገሽጽ ገብታል
ድርጅቱ የተጠቀሰው ቁጥር በጦርነቱ ወቅት በረሃብ ፣ በድህነት እና በበሽታ ምክንያት የሞቱ ሕፃናትን እንደማያካትት ገልጿል
በአፍጋኒስታን ለ20 ዓመታት በተካሄደው ጦርነት 33ሺ የሚጠጉ ሕፃናት ተገድለዋል ወይንም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ይህም በየአምስት ሰዓቱ በአማካይ አንድ ሕፃን ሰለባ መሆኑን አንድ አለምአቀፍ የእርዳታ ድርጅት ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ከፈረንጆቹ 1976 ዓ.ም ጀምሮ በአፍጋኒስታን ውስጥ ለልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው ሕይወት አድን አገልግሎቶችን ማድረጉን የሚናገረው መቀመጫውን በለንደን ያደረገው ሴቭዘችልድረን የተባለው ሰብአዊ ድርጅት አኃዞቹ በልጆች ጦርነቱ በልጆች ላይ ያስከተለው ጉዳት አስከፊ ነበር ብሏል፡፡
ሲጂቲኤን ድርጅቱን ጠቅሶ እንደዘገበው፤በግጭቱ ቀጥተኛ የሕፃናት ጉዳት ከተገመተው ከ32,945 እጅግ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡
ሴቭዘችልድረን የተጠቀሰው ቁጥር ለ20 አመታት በዘለቀው በጦርነቱ ወቅት በረሃብ ፣ በድህነት እና በበሽታ ምክንያት የሞቱ ሕፃናትን” እንደማያካትት ገልጿል፡፡ድርጅቱ ጦርነቱ በአፍጋኒስታን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሰዎች ላይ ያስከለው ስቃይ እጅግ ከፍተኛ ነበር ብሏል፡፡
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ “የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን መውጣት በታሪካችን ትልቁ ውርደት ነው” አሉ
የድርጂቱ የኤሲያ ተወካይ እንደገለጸው በቅርቡ እንኳን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰራዊት በካቡል የመኖሪያ ሰፈር ውስጥ አሸባሪ ነው ብሎ ያሰበውን ለመምታት በወሰደው የድሮን ጥቃት ስድስት ልጆች ተገድለዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ የተጎጂዎች ጎረቤት “ታሊባኖች ይገድሉናል ፣ አይ ኤስ አይ ኤስ ይገድለናል ፣ አሜሪካኖችም ይገድሉናል” ሲሉ ያለቅሳሉ፡፡
አሜሪካ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን ካስወጣች በኋላ ለ20 አመታት ያህል ሲታገል የነበረውና በአሸባሪነት የተፈረጀው ታሊባን ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡ ክስተቱ የአሜሪካን ሽንፈት ያሳየ ነው በሚል የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡