የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ወንጀለኞች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እወስዳለሁ አሉ
የአዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር የወንጀል ላይ ዘመቻቸው የማሸሻያ አካል ነው ተብሏል
የዩናይትድ ኪንግደም እስር ቤቶች አንድ ሽህ ክፍት ቦታዎች ብቻ እንዳላቸው ተነግሯል
ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በዩናይትድ ኪንግደም እስር ቤቶች ውስጥ ብዙ ወንጀለኞች ታስረው ማየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው በወንጀል ላይ ጠንከር ያለ መልዕክት በማስተላለፍ መራጮችን ማበረታታት ይፈልጋሉ ተብሏል።
ጠቅላይ ሚንስትር ሱናክ ወንጀልን ላይ የሚወሰደው እርምጃ ፓርቲያቸው በፈረንጆቹ 2019 ተቃዋሚው ሌበር ፓርቲን እንዲያሸንፉ ያደረገ አጀንዳ አካል አድርገው እመለከተዋለሁ ብለዋል ።
የሱናክ አስተያየት የመራጮችን ድጋፍ እና በተለምዶ በወንጀል ላይ ጠንካራ አቋም የሚወስዱትን የወግ አጥባቂ አማኞችን ድጋፍ ለማቆየት ያተኮረ ነው ተብሏል።
ሱናክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንጀለኞች እስር ቤት መገኘት ወንጀል የመቀነሱ "ሚዛናዊ አመክንዮ" ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ እርምጃው ሁለት ሴት ልጆቻቸውን ለመጠበቅ ከመፈለግ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ብሉምበርግ ሱናክ ብዙ ወንጀለኞችን ከርቸሌ ለመወርወር ያላቸው ፍላጎት የዩናይትድ ኪንግደም እስር ቤቶች አቅም በመዳከሙ ሊደናቀፍ ይችላል ብሏል።
የብሔራዊ የእስር ቤት መኮንኖች ማህበር ሊቀ-መንበር ማርክ ፌርኸርስት እስር ቤቶች ተጣበዋል ብለዋል። በሀገሪቱ አንድ ሽህ የሚጠጉ ቦታዎች ብቻ አሉ ያሉት ሊቀ-መንበሩ፤ በእስር ቤቶች መጨናነቅ ምክንያት አዲስ የሚገቡ እስረኞችበፖሊስ ክፍል ውስጥ መቆየት ሊኖርባቸው ይችላል ብለዋል።
የሀገሪቱ አኃዛዊ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ዩናይትድ ኪንግደም እስከ ሰኔ 2022 በአጠቃላይ 89 ሽህ 520 ታራሚዎች በእስር ቤት አሏት። ከእነዚህም ውስጥ 52 በመቶው ታራሚዎች በእንግሊዝ እና በዌልስ ባሉ እስር ቤቶች "ተጨናንቀው ተመድበዋል" ተብሏል።
በፈረንጆቹ 2026 የእስር ቤቱ ህዝብ ትንበያ ይተነብያል ወደ 98 ሽህ700 ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።