ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት ሙሉ በሙሉ አቋረጠች
ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በመካከላቸው ያለውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ ነበር ስምምነቱን የተፈራረሙት
ፒዮንግያንግ ጠንካራ ሰራዊቷንና ከባባድ የጦር መሳሪያዎቿን ድንበር ላይ እንደምታሰፍር አስታውቃለች
ሰሜን ኮሪያ ከ5 ዓመታት በፊት ከደቡብ ኮሪያ ጋር የተፈራረመችውን ወታደራዊ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ማቋረ,ጧን አስታወች።
ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ በመካከላቸው ያለውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ በማሰብ ነበር ከአምስት ዓመታት በፊት ስምምነቱን የተፈራረሙት።
ለስምምነቱ መቋረጥ መነሻ የሆነውም ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ማክሰኞ የተሳካ የስለላ ሳተላይት የማምጠቅ ስራ ማከናወኗን ተከትሎ እንደሆነም ታውቋል።
- ሰሜን ኮሪያ ሶስተኛውን የስለላ ሳተላይት የማምጠቅ ሙከራ በቀጣይ ቀናት ታደርጋለች
- ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀቻት የወታራዊ ስለላ ሳተላይት ባህር ውስጥ ወደቀች
ሰሜን ኮሪያ የስለላ ሳተላይት ማምጠቋን ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ስምምነቱን ገታ በማድረት በድንበር አካባቢ የምታደርገውን የስለላ በረራ እቀጥላለሁ ማለቷም ታውቋል።
ይህንን ተከትሎም ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ ጠንካራ ሰራዊቷንና ከባባድ የጦር መሳሪያዎቿን ድንበር ላይ እንደምታሰፍር አስታውቃለች።
የሰሜን ኮሪያ መንግስት ባወጣው መግለጫ፤ “ከዚህ በኋላ ወታደሮቻችን በጥር 19 ከደቡብ ኮሪያ ጦር ጋር በተደረሰው ስምምነት አይታጠሩም” ብሏል።
“በምድር ፣ በባህር እና በአየር ላይ ባሉ በሁሉም መስኮች ወታደራዊ ግጭትን ለመከላከል የተወሰዱትን ሁሉንም እርምጃዎች” በማቆም “የበለጠ ኃይለኛ የታጠቁ ሀይሎችን እና አዲስ አይነት ወታደራዊ መሳሪያዎችን” በድንበር አካባቢ እንደሚያሰማራ ቃል ገብቷል።
ደቡብ ኮሪያ “ማሊጊዮንግ-1” የተባለችውን የስለላ ሳተላይት ይዟል ተብሎ የሚታመንበትን ሮኬት ማክሰኞ እለት ስኬታማ በሆነ መልኩ ማምጠቋን አስታውቃለች።
የሰሜን ኮሪያን የስለላ ሳተላይት ማምጠቅ የተቃወሙት የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት በድንበር አካባቢ የክትትል ሥራዎችን ወዲያውኑ እንደገና ለመጀመር ተመወሰናቸውም ይታወሳል።