የኖርዌይ ፓርላማ በዛሬው እለት የቦምብ ጥቃት ዛቻ የደረሰው ሲሆን ፓሊስም በህንጻው ዙሪያ ጥበቃ አጠናክሯል
የኖርዌይ ፓርላማ የቦምብ ጥቃት ዛቻ ደረሰው እንደደረሰው ገለጸ።
የኖርዌይ ፓርላማ በዛሬው እለት የቦምብ ጥቃት ዛቻ የደረሰው ሲሆን ፓሊስም በህንጻው ዙሪያ ጥበቃ አጠናክሯል፤ በአቅራቢያው ያሉ መንገዶችንም ዘግቷል።
በህንጻው ውስጥ በስብሰባ ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች ለቀው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን የፓርላማ አባላት ግን መደበኛ ስራቸውን በመስራት ላይ መሆናቸውን የፓሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ "አሁን በቦታው ነው ያለነው። በርካታ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ሊኖሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ቅኝት በማድረግ ላይ ናቸው"ብለዋል።
በማዕከላዊ ኖርዌይ ራዮት ጊር ወይም ከጥቃት መከላከያ የያዙ ፖሊሶች ወደ ህንጻው የሚያደርሱ መንገዶችን እየዘጉ ይገኛሉ።
በኖርዌይ ፖሊሶች ብዙ ጊዜ ጠብመንጃ ይዘው አይታዩም።
ኖርዋይ የወንጀል ምጥነት ዝቅተኛ ከሆነባቸው የአውሮፓ ሀገራት በቀዳሚነት የምትጠቀስ ነች።
አራት ታጣቂዎች በሩሲያ ሞስኮ አቅራቢያ በተካሄደ የሙዚቃ ድግስ ላይ የፈጸሙት ጥቃት በቅርቡ ከተመዘገቡት አሰቃቂ የሽብር ጥቃቶች አንዱ ነው።
በአፍጋኒስታን ይንቀሳቀሳል የተባለው አይኤስአይኤስ-ኮራሳን የተባለው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ኃላፋነቱን እንደሚወስድ ቢገልጽም፣ ሩሲያ ግን ከጥቃቱ ጀርባ የዩክሬን እጅ አለበት የሚል ክስ አቅርባለች። ዩክሬን ይህን ክስ አስተባብላለች።