ፑቲን ሁሉም ሀገራት ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም ጥያቄ አቅርበዋል
የኒውዩክለር ጦርነትን በማንኛውም ዋጋ ቢሆን ማስወገድ እንደሚገባ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሳሰቡ።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከል ላይ ባተኮረው ጉባዔ ላይንግግር ማድረጋቸውን የሀገራቸው መገናኛ ብዙኃን አርቲ ዘግቧል።
በቀጣይ ኒውክለርን በመጠቀም የሚረግን ጦርነት በየትኛውም መልኩ ማስቀረት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የኒውክለር ጦርነት አሸናፊ የሌለውና ዓለም በፍጹም ሊሄድበት የማይገባ እንደሆነም ነው ቭላድሚር ፑቲን ያሳሰቡት።
ፑቲን ሀገራቸው ከአሜሪካ ለገባችውን ኒውክለርን ያለመታጠቅ ስምምነት እንደምትታመንም የገለጹት።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከልን የሚተገብሩ ሁሉም ሀገራት ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም ጥያቄ አቅርበዋል።
የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከል ውል ዓላማዎች ስርጭቱን መግታት፣ አለመታጠቅና ለሰላማዊ ኃይል መጠቀም የሚሉትን ያጠቃልላል።
ይህንን ስምምነት 192 ሀገራት የተቀላቀሉት ሲሆን ኒውክለር የታጠቁትም በዚህ ስምምነት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው።
ፕሬዝደንት ቫላድሚር ፑቲን አሜሪካን ዋነኛ የሩሲያ ጠላት እንደሆነች ትናንት የሀገራቸው የባሕር ኃይል ቀን ሲከበር ይፋ አድርገዋል።