ፖለቲካ
ኦባሳንጆ የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ከአውሮፓ ሕብረት ም/ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
ኢትዮጵያ ኦባሳንጆ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን በበጎ መቀበሏ ይታወሳል
የህብረቱ ፕሬዘዳንት ከኦባሳንጆ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም በሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውን ተናግረዋል
የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ በመሆን በአፍሪካ ሕብረት የተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ ጉዳይ መክረዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ከኦባሳንጆ ጋር በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ዙሪያ መወያየታቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ቻርለስ ገልጸዋል፡፡
ጦርነቱ እንዲቆም በአስቸኳይ ሊወሰድ የሚገባውን ጥረት በተመለከተም ውይይት ተደርጓል ነው የተባለው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት የአውሮፓ ሕብረት፤ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡