የሀንጋሪ መሪ ወደ ሞስኮ አቅንተው ከፑቲን ጋር መነጋገራቸው የአውሮፓ መሪዎችን አስቆጣ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ የአውሮፓ መሪ በሞስኮ ከፑቲን ጋር ሲገናኝ ይህ የመጀመሪያ ነው

የኔቶ አባል የሆነችው ሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር በትናንትናው እለት ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተወያይተዋል
የሀንጋሪ መሪ ወደ ሞስኮ አቅንተው ከፑቲን ጋር መነጋገራቸው የአውሮፓ መሪዎችን አስቆጥቷል።
የኔቶ አባል የሆነችው ሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በትናንትናው እለት ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የዩክሬን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ መነጋገራቸው ሞስኮን መለማመጥ አያስፈልግም ብለው ሲያስጠነቅቁ የነበሩትን የአውሮፓ መሪዎች አስቆጥቷል።
ሀንጋሪ በየስድስት ወሩ የሚዘዋወረውን የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝደንትነት ተረክባለች። ሀገሪቱ የፕሬዝደንት ስልጣኑን ከተረከበች ከአምስት ቀን በኋላ ኦርባን የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ዘለንስኪን በኪቭ ተገኝተው አነጋግረዋል።
ከዚያ ቀጥሎ ለዩክሬን ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ በማድረግ ጉዳይ የሚመክረው የኔቶ ሰብሰባ ጥቂት ቀናት ሲቀረው "ለሰላም ተልእኮ" ወደ ሞስኮ አቅንተዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ የአውሮፓ መሪ በሞስኮ ከፑቲን ጋር ሲገናኝ ይህ የመጀመሪያ ነው።
የኦርባን የሞስኮ ጉዞ በሌሎች የአውሮፓ መሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበበት ሲሆን ዩክሬን ስለጉዞው ቀድማ መረጃ እንዳልደረሳት ገልጻልች።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ቮን ደር ለይን በዩክሬን ፍትህ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ መንገድ የሚያመቻቸው የ27 የአውሮፓ ሀገራት አንድነት እና ውሳኔ ብቻ ነው ብለዋል።
"መለማመጥ ፑቲንን አያስቆመውም" ሲሉ በትዊተር ገለጻቸው ጽፈዋል።
ኦርባንን በክሬሚሊን የተቀበሉበት ፑቲን ሰላም ጠቃሚ መሆኑን ተናግረው፣ ነገርግን ዩክሬን ሁለት አመት ከግማሽ ያስቅጠረው ጦርነት እንዲያቆም አትፈልግም ብለዋል።
"በተጋጋሚ እንደተናገርኩት ግጭቱን በውይይት ለመፍታት ሁልጊዜም ዝግጁ ነን። ይሁን እንጅ በሌላኛው ወገን (በዩክሬን) በኩል ችግሩን በዚህ ለመፍታት ችላ የማለት ዝንባሌ አለ" ሲሉ ፑቲን የለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ፑቲን ባለፈው ወር ዩክሬን ወደ ኔቶ የመቀላቀል እቅዷን ከተወች እና ሞስኮ የይገባኛል ጥያቄ የምታነሳባቸውን አራት ግዛቶች ሙሉ በሙሉ የምታስረክብ ከሆነ ሞስኮ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻዋን"እንደምታቆም ተናግረው ነበር። ኪቭ ይህን የፑቲንን ሀሳብ ወዲያውኑ ነበር ውድቅ ያደረገችው።