በፓሪስ ኦሎምፒክ ተጠባቂ የአትሌቲክስ ውድድሮች መካሄድ ጀምረዋል
ዛሬ ጠዋት በተካሄደው የ20 ኪሎሜትር እርምጃ ውድድር ኢትዮጵያዊው ምስጋና ዋኩማ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ 58 ሜዳልያዎችን አግኝታለች
የፓሪስ ኦሎምፒክ ስድስተኛ ቀኑን ሲይዝ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተጀምረዋል።
ጠዋት ላይ የ20 ኪሎሜትር እርምጃ ውድድር ሲካሄድ ኢኳዶራዊው አትሌት ብሪያን ፒንታዶ አሸናፊ ሆኗል።
የ29 አመቱ አትሌት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰአት ከ18 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ፈጅቶበታል።
የብራዚሉ ካዬ ቦንፊም እና ስፔናዊዎ የአለም ሻምፒዮን አልቫሮ ማርቲን የብር እና የነሀስ ሜዳልያ አግኝተዋል።
ኢትዮጵያዊው ምስጋና ዋኩማ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የፓሪስ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሲቀጥሉ ነገ ምሽት 4 ስአት ከ20 ላይ የሚደረገው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይጠበቃል።
የቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በውድድሩ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ እና ግማሽ ፍፃሜ ውድድሮች ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄዱ ሲሆን፥ ሰኞ ምሽት 4 ሰአት ከ10 የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል።
የፍፃሜ ውድድሮች መርሀግብር
ሀምሌ 29 2016
ምሽት 4 ሰአት ከ10
- 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)
ምሽት 4 ሰአት ከ45
- 800 ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)
ሀምሌ 30 2016
ምሽት 3 ሰአት ከ50
- 1500 ሜትር ፍፃሜ (ወንዶች)
4 ሰአት ከ10
- 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ (ሴቶች)
ነሀሴ 1 2016
ምሽት 4 ሰአት ከ40
- 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ (ወንዶች)
ነሀሴ 3 2016
ምሽት 3 ሰአት ከ55
- 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)
ነሀሴ 4 2016
ጠዋት 3 ሰአት
- ወንዶች ማራቶን ፍፃሜ
ምሽት 3 ሰአት
- ወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ
ምሽት 3 ሰአት ከ25
- 1500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ
ነሀሴ 5 2016
ጠዋት 3 ሰአት
- ሴቶች ማራቶን ፍፃሜ
በ1956 በሜልቦርን ኦሎምፒክ ተሳትፎዋን አሀዱ ያለችው ኢትዮጵያ በታሪካዊው መድረክ 58 ሜዳልያዎችን አግኝታለች።
ያገኘቻቸው 23 የወርቅ፣ 12 የብር እና 23 የነሀስ ሜዳልያዎች ሁሉም በአትሌቲክስ ውድድሮች የተገኙ ሲሆን 11 አትሌቶች ከአንድ በላይ የኦሎምፒክ ሜዳልያ አግኝተዋል።
በፓሪስ ኦሎምፒክስ ምን ያህል ሰኬታማ ትሆናለች የሚለው ከዛሬ ምሽቱ የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድ ጀምሮ የሚታይ ይሆናል።