ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ፕ/ት ኡሁሩ ኬንያታ የሐዋሳ-ሞያሌ መንገድን መርቀው ከፍተዋል
ዛሬ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና በኬንያ ፕ/ት ኡሁሩ ኬንያታ የተመረቀው 500 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውና የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ ኮሪደር አካል የሆነው መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስር ነው፡፡
ይኸው የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ወጪው ከአፍሪካ ልማት ፈንድ የተገኘ ነው፡፡
የአዲስ አበባ-ሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ አዲስ አበባን ከካይሮ፣ ጋቦሮኒ፣ ኬፕ ታውን እና ኬንያ-ሞምባሳ የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ደቡብ ሱዳንን-ከኬንያ ላሙ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ ጋር በላሙ ወደብም ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የኬንያው ዋነኛ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋም በላሙ ወደብ ጉብኝት ላይ ተሳትፈዋል፡፡
የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳንን በጋራ የሚያስገነቡት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡
ሁለቱ መሪዎች የድንበር ጸጥታን ጨምሮ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይም ይመክራሉ፡፡