ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፖለቲከኞች ጋር በካርቱም ተወያዩ
ሱዳናዊያን ካለማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት የፖለቲካ ችግራቸውን መፍታት ስለሚችሉበት ሁኔታ መወያየታቸው ተገልጿል
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዛሬ ረፋድ ለይፋዊ ጉብኝት ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፖለቲከኞች ጋር በካርቱም ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ድ/ር) ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ለይፋዊ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም መግባታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሱዳን ካርቱም ሲደርሱም የሱዳን ሉአላዊ ም/ቤት ሌተናል ጅነራል አብደልፈታህ አልቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
- ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ድንበራቸውን ጉዳይ በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ተገለጸ
- "በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ላይ የሚፈጠሩ ክስተቶች የሁለቱን ሀገራት ትስስር አያቋርጡም" ጠ/ሚ ዐቢይ
ጠቅላይ ሚንስትሩ እና የልዑካን አባላቸው ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝዳንት ጀነራል አልቡርሀን ጋር ተገናኝተዋል።
እንዲሁም ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሱዳን ከነጻነት እና እኩልነት ሀይሎች ጋርም እንደመከሩ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከናሽናል ኡማ ፓርቲ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ፋድላላህ ባርማህ ናስር ጋርም ተወያይተዋል ተብሏል።
የሱዳን ወቅታዊ የፖለቲካ ችግሮች የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳ ነበር የተባለ ሲሆን ሱዳን ከውጭ ጣልቃ ገብነት በጸዳ መንገድ የፖለቲካ ችግራቸውን እንዲፈቱ ማድረግ ሌላኛው የውይይታቸው አጀንዳ እንደሆነ ተገልጿል።
ሱዳን ከገጠማት የወቅቱ ፖለቲካዊ ችግር እንድትወጣም ኢትዮጵያ ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሱዳን ጉብኝት በድንበር ውዝግብ ምክንያት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከሻከረ በኋላ የመጀመሪያ ነው።