በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋን ክልል በተፈጠረ የጎሳ ግጭት 30 ሰዎች ሞቱ
ምዕራብ ኮርዶፋን ክልል ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ ደም አፋሳሽ የጎሳ ግጭት ተከስቷል
ባለፉት ሁለት ዓመታት ምእራብ ኮርዶፋን ክልል በሀመርና ሚሴሪያ ጎሳዎቸ መካከል በተደጋጋሚ ግጭች ሲከሰቱ ተስተውሏል
በሱዳን ምእራብ ኮሮዶፋን ክልል በተከሰተ ደም አፋሳሽ የጎሳ ግጭት ቢያንስ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ ምእራብ ኮርዶፋን ክልል በተፈጠረው ደም አፋሳሽ የጎሳ ግጭት ከሞቱ ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸውም ተመላክቷል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ምእራብ ኮርዶፋን ክልል በሀመር እና ሚሴሪያ ጎሳዎቸ መካከል ከመሬት ይገባኛል ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ግጭች ሲከሰቱ ተስተውሏል።
የምእራብ ኮርዶፋን ክልል አስተዳደር ባሳለፍነው ነሃሴ ወር የወሰን ማካለል ያደረገ ቢሆንም እርምጃው አቡ ዛሃድ በተባለ አካባቢ ግጭት እንዲከሰት አድርጎ እንደነበረም ይታወሳል።
ባሳለፍነው ህዳር ወር አጋማሽም ኢብራሂም በተባለ ገጠራማ አካባቢ ከውሃ ጋር በተያያዘ በሀመር ጎሳ ስር በሚገኙት “ባ ፈድል” እና “ባኒ በድር” በተባሉ ዘሮች መካከል ገጭት ተከስቶ እንደነበረ አይዘነጋም።
ከውሃ ጋር ተያየዝ በተከሰተ ግጭትም 20 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውም ተነግሯል።
በሱዳን በተለያዩ ጊዜያት የጎሳ ግጭቶች የሚስተዋሉ ሲሆን፤ ከጀርባቸውም ስማቸው ያልተገለፀ የታጠቀ ኃል እንዳለ የሱዳን መከንግስት በተደጋጋሚ ስገልጽ ይስታዋላል።