"በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ነገር ይቋጫል፤ ኢትዮጵያ ሰላም ትሆናለች"- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የሚደረገው የሰላም ድርድር የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር ይጠበቃል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “በአጭር ጊዜ ውስጥ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ለሰላምና ለልማት እንቆማለን" ብለዋል
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ነገር አብቅቶ ኢትዮጵያ ሰላም ትሆናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡራዩ ከተማ የተገነባውን የባለ ልዩ ተሰጥዖ ተማሪዎች ልማት ማዕከልን መርቀው በከፈቱበት ወተቅ ነው ይህንን ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር "በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ያበቃል፣ሰ ላም ይሰፍናል፣ለዘላለም እየተዋጋን አንቀጥልም” ብለዋል።
“በአጭር ጊዜ ውስጥ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ለሰላምና ለልማት እንቆማለን" ሲሉም ተናረዋል።
ኢትዮጵያውያን በዘርና በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በጋራ ለሀገር ብልጽግና እንዲረባረቡም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከቀናት በፊት ባወጣው ባወጣው መግለጫ ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን ገልጾ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማረጋገጥ በትግራይ ክልል የሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎችን እና የፌደራል ተቋማትን እንደሚቆጣጠር ማሳወቁ ይታወሳል።
መንግስት፤ የመከላከያ ሰራዊት ሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተሞችን መቆጣጠሩን እና በቅርቡ የሰብዓዊ ድጋፎች እና የተቋረጡ መሰረታዊ አልግሎቶችን ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል መንግስት እና ህወሓት የፊታችን ሰኞ በደቡብ አፍሪካ እንደሚደራደሩ ተገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ የፌደራል መንግስትን እና ህወሀትን ለማደራደር ቦታ ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል።
የህብረቱን ድርድር ሁለቱም ወገኖች በወቅቱ መቀበላቸውን ያሳወቁ ቢሆንም ዘግይቶ በወጣ መረጃ ደግሞ ድርድሩ በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙ አይዘነጋም።
የጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት የፌደራል መንግስት እና ህወሀት በደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ድርድር የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2022 እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለጉቴሬሰ ንግግር በሰጡት ምለሽ፤ “የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሌላ መልክ ለመቀባት ለሚፈልጉት አካላት በኢትዮጵያ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር የለም” ብለዋል።