የፖላንድ ሴቶች የዩክሬን ሴቶች ባሎቻቸውን ይነጥቁናል በሚል ስጋት እንዳለባቸው ገለጹ
የዩክሬን ሴቶች በፖላንድ እንዳይጠለሉ ያለው ፍላጎት እየጨመረ ነው ተብሏል
ወጣት ዩክሬናዊያንን የሚፈልጉ ፖላንዳዊያን ወንዶች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ተገልጿል
የፖላንድ ሴቶች በዩክሬን ሴቶች ባሎቻቸውን የመነጠቅ ስጋት እንዳለባቸው ገለጹ።
ሩሲያ ለአንድ ሳምንት በሚል ለልዩ ዘመቻ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ከላከች 18ኛ ወሩ ላይ ይገኛል።
የሩሲያ ጦር ጥቃቷን ማስፋፋቷን ተከትሎም ከ15 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን መኖሪያ ቤቶቻቸውን በመልቀቅ ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።
የዩክሬን ጎረቤት የሆነችው ፖላንድ ብዙ ዜጎች የተጠለሉ ሲሆን በሀገሬው ሴቶች ግን እንደ ስጋት ታይተዋል።
የፖላንድ ሴቶች ዩክሬናዊያን እንስቶች ባሎቻችንን ሊወስዱብን ይችላሉ እሚለው ስሜት እየጨመረ መምጣቱን የዋርሶው ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በዚህ ምክንያትም ዩክሬናዊያን እንስቶች ወደ ፖላንድ እንዳይመጡ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር መጨመሩ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ወጣት ዩክሬናዊያንን የሚፈልጉ ፖላንዳዊያን ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ተገልጿል።
በተለይም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ወጣት ዩክሬናዊያን ሴቶችን የሚፈልጉ ማስታወቂያዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው ተብሏል።
ከወራት በፊት ወደ ብሪታንያ ያመሩ ዩክሬናዊያን የሰው ባል ቀምተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ትችቶችን ማስተናገዳቸው አይዘነጋም።
የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ጦር ጥቃት ምክንያት እየተጠቁ ነው በሚል ለዩክሬናዊያን ስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት ላይ ናቸው ተብላል።