አንድ የፑቲን ጠባቂ እድሜው 35 ዓመት ሲሞላው ከስራ ይሰናበታል ነው የተባለው
ሰሞኑን የምዕራባውያን የእግር እሳት እንደሆኑ የሚነግረላቸው የሞስኮው ሰው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን በጀመሩት ወታዳራዊ ዘመቻ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀዳሚው አጀንዳ ከሆኑ ሰነባብተዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን የጀመሩት ጦርነት አጀንዳ የሆኑትን ያክል፤ በርካታ የዓለም አቀፍ የሚድያ አውታሮች ስለ ስብዕናቸው እና የህይወት ዘይቤያቸው ሲናገሩም ይስተዋላል።
የቀድሞ የሩሲያ የስለላ ተቋም (ኬጂቢ) አባል የነበሩት ቭላድሚር ፑቲን፤ ለብዞዎች ግልጽ ካልሆነው የቤተሰብ ሁኔታ አንስቶ ስለሚደረግላቸው እጅግ የተራቀቀና ከሌሎች የዓለም መሪዎች የተለየ የደህንነት ጥበቃም በርካቶች ሲናገሩ ይደመጣል።
በተለይም “ፍጹም የመድከም ስሜት አይታይባቸውም” ስለሚባሉት የፑቲን ጠባቂዎች በርካታ ነገሮች ይባላሉ።
ቭላድሚር ፑቲን በማንኛውም ሁኔታ ላይም ቢሆኑ ላብ የማያጠምቃቸው እና ቅዝቃዜ የማይበግራቸው እንዲሁም የፕሬዚዳንቱን እያንዳንዷን የእግር ኮቴ እንቅስቃሴና እስትንፋስ በትኩረትና ቅርበት የሚከታተሉ “ባላባቶች” የተሰኙ ጠባቂዎች አላቸው።
ፑቲን ሊሄዱበት ካሰቡ እንደሁም ባሉበት ስፍራ ሁሉ እነዚህ ጠባቂዎች (የደህንነት ቡድን አባላት) አሉ።
ሩሲያ ቢዮንድ የተሰኘ ድረ ገጽ እንዳስነበበው፤ የፑቲን ጠባቂዎች፤ ፕሬዝዳንቱ ላይ ሊቃጡ ይችላሉ የሚሏቸውን አደጋዎች እንዲሁም በጉብኝት ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ መሬት መንቀጥቀጥና ጎርፍ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋዎች የመተንተን ብቃት ያላቸው ሁለገብ ጠባቂዎች ናቸው።
ሌላው አስገራሚው ነገር በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አማካኝነት በፑቲን ለጠባቂነት የሚመረጡት ጠባቂዎች በሌላው ዓለም እንደተለመደው ከወታደር ቤት የተመለመሉ አለመሆናቸው ነው።
ሩሲያ ቢዮንድ አንድ የቀድሞ የፑቲን ጠባቂ ነግሮኛል ብሎ እንደጻፈው ከሆነ "የፕሬዝዳንቱ ጠባቂዎች በየተራራው የመዝለልና አድፍጦ የመወጋት ልምድ ሊኖራቸው ይገባል የሚለው ለፑቲን አይሰራም" ይላል።
የቀድሞ የፑቲን ጠባቂ " የትግል ልምድ ጠቃሚ ነው ነግር ግን ለእኛ ስራ እምብዛም አይደለም፣ የጠባቂዎች ስራ ታዋቂውን ሰው ከማይታይ ሰው መጠበቅ እንዲሁም ጥቃት የሚያድረስ አካል ካለም ጥቃት መሰንዘር ብቻ ነው" ሲልም አክሏል።
የፕሬዝዳንቱን ደህንነት መጠበቅ ቀዳሚው የጠባቂዎቹ ኃላፊነት መሆኑን ያስረዳው የቀድሞ ጠባቂ፤ ጠባቂዎች በፕሬዝዳንቱ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል "ኦፕሬሽናል ሳይኮሎጂ" ሊኖራቸው እንደሚገባም አንስቷል።
የፑቲን ጠባቂ ለመሆን ከ35 ዓመት በታች፣ ከ175 እስከ 190 ሴንት ሜትር ቁመት እንዲሁም ከ75 እስከ 90 ኪ.ግ ክብደት መሆን እንደሚያስፈልግም ተናግሯል።
ይህ ብቻ አይደለም የፑቲን ጠባቂዎች የውጭ ቋንቋዎች የመረዳት አቅም ያላቸውንና ፖለቲካን በደምብ የሚገነዘቡ ሊሆኑ እንደሚገባና ይህም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፑቲን ጋር ቀርበው የሚያወጉ ሰዎች ማንነት ለማወቅ እንደሚያስችላቸውም አስረድቷል።
ሩሲያ ቤዮንድ የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች የመቋቋም አቅምና በስፖርት የዳበረ ሰውነት ያላቸው፣ ወፍራም ልብሶች እንቅስቃሴያቸውን ሊያደናቅፉ የችላሉ በሚል ከፍተኛ ቅዝቃዜን ለመቋቋም እና ቀላል ካፖርት እንዲለብሱ የሰለጠኑ መሆናቸውም ይነገራል።
ከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ሆነው ላብ አይታይባቸውም ነው የሚባልው፡፡
የፊዚዮሎጂ ሂደቶችን የሚነኩ መድኃኒቶችን እንደሚጠቀሙ የሚነገርላቸው የፑቲን ጠባቂዎች አልፎ አልፎ ጭንቀታቸውን ለማስታገስ ሲጋራ እንዲያጨሱ ይፈቀድላቸዋል ይፈቀድላቸዋልም ነው የተባለው።
አንድ የፕሬዝዳንቱ ጠባቂ እድሜው 35 ዓመተት ከሞላው ከሞላው ከስራው በጡረታ እንደሚሰናበትም ሩሲያ ቤዮንድ በደርረ ገጹ አስነብቧል።