6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀመሮ እየተካሄደ ይገኛል
ዘግይተው በጀመሩ ጣቢያዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ነው ብለዋል።
በመላ ሀገሪቱ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ላይ የጀመረ ሲሆን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ ነበር መርሃ ግብር የወጣለት።
ነገር ግን ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ጣቢያዎች በመኖራቸው፣ በቁሳቁስ እጥረት እና በሌሎች ምክንያቶች በምርጫ ጣቢያዎች እስካሁን ረጃጅም ሰልፎች ይስተዋላሉ።
የቦርዱ የኮሙኒክሼን አማካሪ ሶሊያና ሽመለስ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ የድምጽ መስጫ ሰዓቱ መራዘሙን አስታውቀው፤ ዘግይተው በጀመሩ ጣቢያዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ነው ብለዋል።
ስለዚህ በሀሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ቀጥሎ ይካሄዳል ብለዋል።
ኢትዮጵያ 6ኛው ዙር የተወካዮች ምክርቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ በዛሬ እለት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት የተጀመረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ፤ በመላ በ673 የምርጫ ጣቢያዎች እየተካሄደ ይገኛል።
ምርጫ የማይካሄደው በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 አይካሄድም፡፡
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ጻግሜ 1 እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።
በምርጫ ከ38 ሚሊዮን ህዝብድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል፤45 የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲሰማሩ ቦርዱ ገልጾ ነበር።