ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ “ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ
አባ ፍራንሲስ፤ እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ “ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው" መሆኑም ተናግረዋል
ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግ “ፍትሃዊ ጦርነት” ነው ብለዋል
የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ፤ ራሷን በመከላከል ላይ ላለችው ዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ “በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ።
ሊቀ ጳጳሱ ይህን ያሉት ከሶስት ቀን የካዛኪስታን ቆይታ ሲመለሱ በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው በነበረቻው 45 ደቂቃ የፈጀ ቃለ ምልልስ ላይ ከአንድ ጋዜጠኞች “ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መላካችው ትክክል ነው?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።
አባ ፍራንሲስም “ይህ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ፤ ነገር ግን መርሆችን ባከበረ መልኩ የሚደረግ ከሆነ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት ያለው ውሳኔ ነው” ብለዋል።
የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግና በመርህ ደረጃም “ፍትሃዊ” የሚባል ጦርነት መሆኑ ለዚህም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሃሳባቸው እንድትጋራ የሚያስችል ማብራሪያም መስጠታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል።
"እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው" ሲሉም አክለዋል። ሊቀ ጳጳሱ የሩሲያ - ዩክሬን ጦርንት እንዲያበቃ ምኞታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
ጦርነቱ እንዲቆም “ዩክሬን ለውይይት ክፍት እንድትሆን” የጠየቁት ሊቀ ጳጳሱ፤ በቅርቡ ከዩክሬን ጋር ምንም ዓይነት የድርድር ተስፋ እንደማይኖር ስለገለጸችው ሩሲያ ግን ያሉት ነገር የለም።
ያም ሆኖ ሊቀ ጳጳስ ፍራሲስ፤ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝቶ ለመምከር ፍላጎት እንዳላቸው ባሰለፍነው ግንቦት ወር አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም።
ሊቀ ጳጳሱ፤ ከጣሊያኑ ኮሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ሞስኮው መምጣት እፈልጋለሁ ሲሉ ለፑቲን መልዕክት መላካቸውንም ተናግረው ነበር።
መልዕክቱ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በተጀመረ በ20ኛው ቀን የተላከ መሆኑንም ነበር ሊቃ ጳጳስ ፍራንሲስ የተናገሩት።
የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ጥያቄ ብያቀርቡም፤ በክሬምሊን ባለስልጣነት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።