ፕሬዝዳንቷ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ወደ ኬንያ ያቀኑት
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኬንያ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንቷ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ወደ ኬንያ ያቀኑት፡፡ ናይሮቢ በደረሱ ጊዜም በፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
መሪዎቹ በሁለትዮሽ እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ቢሮ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
ፕሬዝዳንቷ በምን ምክንያት ወደ ናይሮቢ ሊያመሩ እንደቻሉ በራሳቸውም ሆነ በጽህፈት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ፕሬዝዳንቷ በምን ምክንያት ወደ ናይሮቢ ሊያመሩ እንደቻሉ በራሳቸውም ሆነ በጽህፈት ቤታቸው በኩል የተገለጸ ነገር የለም፡፡
ኬንያ 15 አባላት ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ናት፡፡