ኢትዮጵያውያን ለሰላምና ለእውነተኛ እርቅ መንገድ እንዲያመቻቹ የኬንያው ፕሬዝዳንት ጥሪ አቀረቡ
ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሳታፊ የሆኑት አካላት ሁሉ ጦርነቱን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል
የቀጠለው ግጭት ታላቋ ን ሀገር በርካታ ነገሮች እየነጠቀ መሆኑን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል
ኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያውያን ሰላምን ተቀብለው ለእውነተኛ እርቅ መንገድ እንዲጠርጉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ሁሉ ጦርነቱን እንዲያቆሙም ተማጽኗል።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልክት ማምሻው ባወጡት መግለጫ፤ ኬንያ ተኩስ ማቆምን እና ለመደራደር መንገድን ማመቻችት በሚሉ ጉዳች ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያቀረቡትን ጥሪ እንደምትጋራ አስታውቋል፡፡
“የቀጠለው ግጭት የኢትዮጵያን ህዝብ እየዘረፈ እና የዚህ ታላቅ ህዝብ ባህልና ስልጣኔ ውስጥ ያለውን ክብር እያሳጣ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
"አስተማማኝ ሰላም የሚሰፍነው እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን የምትሆነው ሁሉም የኢትዮጵ አካላት ዘላቂ በሆነና በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ባለው መንገድ ፈተናዎችን ማለፍ ሲችሉ ብቻ ነው" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለው "በእርግጥ ሁሉንም ያሳተፈና በመስማማት መንፈስ የሚካሄደው ሀገራዊ ውይይት፤ በግጭቱ ምክንያት ለተጎዱ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ማህበረሰቦች ያለውን ሸክም ከማቅልለ አንጻር ከፍተኛ እገዛ ደርጋል" ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ፣ የቀጠናው እንዲሁም የአህጉሪቱ ብልፅግና፤ ዘላቂ በሆነ ሰላም እና ደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብለዋል።
“አንድ ላይ ሆነን የተሻለ ዓለም መፍጠር እንችላለን”ም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።
ኬንያ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ የተለያየ ጥረት በማድረግ ላይ ያለች ሀገር እንደሆነች ይገለጻል።
ኢጋድ ዋና ጸኃፊ ዶ/ር ወርቅነህ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆት ከወር በፊት በኬንያ ሞምባሳ በተካሄደው ሁለተኛው የኢጋድ ዓመታዊ ስብሰባው ላይ መግለጻቸው ይታወሳል።