አወዛጋቢ ቃለ መጠይቅ የሰጡት በጀርመን የዩክሬን አምባሳደር ተባረሩ
ዲፕሎማቱ በዓለም ጦርነት ከጀርመን ሃይሎች ጋር የተባበሩትን የሀገራቸውን ሰው ደግፈዋል ተብሏል
አምባሳደሩ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ዩክሬይንን በጀርመን ወክለዋል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ከሰሞኑ አወዛጋቢ ቃለ መጠይቅ የሰጡትን ዲፕሎማት አባረሩ።
ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሃላፊነታቸው ያነሷቸው በጀርመን የነበሩትን አምባሳደር ነው።በጀርመን የሚገኙት የዩክሬን አምባሳደር አንድሬ ሜልኒክ ከሃላፊነታቸው የተነሱት ከሰሞኑ በሰጡትና አወዛጋቢ ነው በተባለው ቃለ ምልልስ ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
አምባሳደሩ በሰጡት ቃለ መጠይቅ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ብሔርተኛ የነበሩትንና የፋሽስት ሃሳብን ይደግፉ የነበሩትን የዩክሬን ቀኝ ዘመም ድርጅት መሪስቴፓን ባንደራን ተከላክለዋል።
እኒህ ቀኝ ዘመም የነበሩት መሪ በወቅቱ ዩክሬንን ከወረሩት የጀርመን ሃይሎች ጋር መተባበራቸው በታሪክ ተጠቅሷል ።
ባንደራ የጀርመን ሃይሎች በፈጸሙት ግድያ ላይ በቀጥታ ያልተሳተፉት በ 1941 ዩክሬይን ውስጥ በመታሰራቸው እንደሆነ ይገለጻል። አምባሳደር ሜልኒክ ባንደራ እንደዚህ አደረጉ የሚባለው ነገር በሚገባ ያልተረጋገጠ እንደሆነ መግለጻቸውን ተከትሎ ንግግራቸው አወዛጋቢ ሆኗል።
በአምባሳደር ሜልኒክ ቃለ ምልልስ የተከፉት የጀርመን ባለስልጣናት እና በጀርመን የእስራኤል ኤምባሲ ቁጣቸውን ገልጸዋል።ከዚህ በተጨማሪም ሁለት የፖላንድ ሚኒስትሮች በዲፕሎማቱ ንግግር ማዘናቸውን መናገራቸው ተገልጿል።
ይህ የአምባሳደሩ ንግግር ከሩሲያ ጋር ውጊያ ውስጥ ላለችው ዩክሬይን በእንቅርት ላይ እንዳይሆንባት በመስጋት ከሃላፊነት አንስታለች።
አምባሳደሩ በፈረንጆቹ ከ 2014 ጀምሮ በጀርመን ዩክሬንን ወክለው ነበር።