ኢትዮጵያ ከአዲሱ የሶማሊያ መንግስት ጋር በተለያዩ ደረጃዎች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ተወያይተዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ እንዲሆን በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ገለጹ።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ አዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ ከሚመራው የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነትን ገልጸዋል።
በተለይም የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ እንዲሆን አብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ትኩረት ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ኢትዮጵያ የተሻለች ሶማሊያን ለማስቻል ለተከፈለው መስዋዕትነት አድናቆታቸውን እና ሁለቱ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ችግሮች ለመፍታት የትብብር አስፈላጊነትን ማመላከታቸውን ጽህፈት ቤቱ ስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአዲሱ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አስተዳደር ጋር በተለያዩ ደረጃዎች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፤ በተለይም ለኢኮኖሚ ዕድገት አጽንዖት ሰጥተዋል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በመቀጠልም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎብኘተዋል።
በዚህም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ፕሬዝዳንቱንና ለልዑካን ቡድናቸውን የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ለእንግዶቹ አስጎብኝተዋል።