ፕሬዝዳንት ፑቲን ስንዴ የጫኑ መርከቦች ወደ ተቸገሩ ሀገራት ብቻ እንዲጓጓዙ እንደርጋለን አሉ
ከዩክሬን ከተነሱ ስንዴ የጫኑ መርከቦች ውስጥ 30 በመቶው ብቻ ወደ ድሃ ሀገራት መጓጓዙን ተመድ ገልጿል
ከዩክሬን ወደ በለጸጉ ሀገራት የገቡ ምርቶች ለቤት እንስሳት ቀለብ መዋላቸውን ተመድ ገልጿል
ፕሬዝዳንት ፑቲን ስንዴ የጫኑ መርከቦች ወደ ተቸገሩ ሀገራት ብቻ እንዲጓጓዝ እንደርጋለን አሉ፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው የምስራቅ ሀገራት የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ባደሩጉት ንግግር ከዩክሬን ስንዴ ከተጫኑ 87 መርከቦች መካከል 85ቱ ወደ አውሮፓ ሀገራት መጓጓዛቸውን ገልጸው ነበር፡፡
ፑቲን ምዕራባውያን ሀገራት ራስ ወዳዶች ናቸው ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ምዕራባዊያን ለራሳቸው ፍላጎት ካልሆነ በቀር ለተቀረው ዓለም ግድ የላቸውም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ዓለማችን ወደ ብዙ ችግሮች እየገባች ያለችው በነዚህ ምዕራባውያን ሀገራት ምክንያት እንደሆነም አክለዋል።
ሩሲያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር በዩክሬን የጀመረችውን ጦርነት ምክንያት በማድረግ በሞስኮ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ለዓለም ምግብና ነዳጅ ዋጋ መጨመር ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑም ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል።
ሩሲያ በተመድ እና ቱርክ አደራዳሪነት መሰረት የምግብ ችግር ወዳለባቸው ሀገራት ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች እንዲጓጓዝ ብታደርግም አብዛኞቹ የስንዴ መርከቦች የምግብ ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች ሳይሆን ወደ አውሮፓ መጓጓዛቸውንም ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ከዩክሬን ወደብ አህል ከጫኑ 87 ሁለት መርከቦች ውስጥ ሁለቱ ብቻ የምግብ ችግር አለበት ወደ ተባለው አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መጓጓዛቸውን ጠቅሰዋል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የሩሲያ አቻቸው ንግግር ትክክል መሆኑን አረጋግጠው ጉዳዩ ሊስተካከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከዩክሬን የእህል ጫኝ መርከቦች የምግብ ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች ከቱርክ እና ሩሲያ ጋር የሚነጋገረው የተመድ ቢሮ በበኩሉ ከዩክሬን ከተነሱ እህል ጫኝ መርከቦች ውስጥ 30 በመቶው ብቻ ወደ ድሃ ሀገራት መጓጓዛቸውን ገልጿል፡፡
አብዛኞቹ እህል የጫኑ መርከቦች ወደ አውሮፓ መግባታቸውን የጠቆመው ተመድ አህሉ በአብዛኛው ለቤት እንስሳት እና ለቤተ ሙከራ አገልግሎት መዋላቸውንም አስታውቋል፡፡
ይሄንንም ተከትሎ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቱርክ እና ተመድ ጋር ብቻ በመነጋገር ከዩክሬን ወደቦች የሚነሱ እህል ጫኝ መርከቦች የምግብ ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች ብቻ እንዲጓጓዙ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡