ሩሲያ ወታደራዊ ተልዕኮው የሚያበቃው ግቡን ሲመታ እንደሆነ ገልጻለች
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዘመናዊቷ ሩሲያ ዕጣ ፋንታ የሚወሰነው የቀድሞ ግዛቶቿን መመለስና ማጠናከር መሆኑን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በወጣቶች ስብሰባ ላይ የሀገራቸውንና የዓለምን ሁኔታ በተመለከተ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ፤ ሩሲያ ታሪካዊ መሬቷን እንደምታስመልስና ይህንንም እንደምታጠናክር አስታውቀዋል።
ሀገራቸው የቀደመ ግዛቶቿን እንደምታስመልስ እርግጠኛ መሆኗን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ስለሀገራቸው ኢኮኖሚም ንግግር ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ሩሲያ ዝግ ሀገር እንደማትሆን የገለጹት ፑቲን የዋጋ ንረት ምዕራባውያን በስህተታቸው ያመጡት እንደሆነም ነው ያስታወቁት።
የሩሲያ ንጉሰ ነገስት የነበሩትና የሩሲን ግዛት ያጠነከሩት ፔተር ዘግሬትን ያስታወቀሱት ፑቲን የዘመናዊቷ ሩሲያ ዕጣ ፋንታ ከቀደመው ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ያለው የዋጋ ንረት የተከሰተው በምዕራባውያን ስህተት ምክንያት እንደሆነ ያነሱት ፑቲን እነሱ ሌሎች ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ ብለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ጀመርኩት ያለችው “ወታደራዊ ተልዕኮ” የሚጠናቀቀው ግቡን ሲመታ መሆኑን አስታቀውቃለች። የሩሲያ ቤተ መንግስት (ክሬምሊን) ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፒስኮቭ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለተልዕኮው አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን መዘርዘራቸውን ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ሩሲያ ወታደራዊ ተልዕኮ እያደረገች መሆኑን ብትገልጽም ምዕራባውያን ግን ሩሲያ ዩክሬንን እንደወረረች እየገለጹ ነው። ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ከገቡ 100 ቀናት አልፈዋል።