ኢማኑዔል ማክሮን ሃገራቸው “የአስታራቂነት ሚና” እንደምትጫወት ተናግረዋል
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፑቲን በዩክሬን ጉዳይ “ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል“ ሲሉ ተናገሩ፡፡
ማክሮን በዩክሬን ምድር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ጉዳይ የፑቲን 'ታሪካዊ' ስህተት ቢኖርም ሩሲያ መዋረድ የለባትም ብለዋል፡፡
ማክሮን ለጋዜጦች በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ ጦርነቱ ቆሞ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ አስፈላጊውን ሁሉ የአስታራቂነት ሚና እንወጣለን ሲሉም ተናግረዋል።
"እኔ እንደማስበው እና እንደነገርኩት ፑቲን ለህዝቡ፣ለታሪክ እንዲሁም ለራሱ ታሪካዊ እና መሰረታዊ ስህተት እየሰራ ነው" ያሉት ማክሮን፤ ዲፕሎማሲያዊ መውጫ መንገድን ማፈላለግ እንጂ “ሩሲያን ማዋረድ የለብንም” ሲሉም አሳስበዋል።
ፈረንሳይ አስታራቂ ሚና እንደሚኖራት እርግጠኛ ነኝ ሲሉም አክለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
ሞስኮ በየካቲት ወር በዩክሬንን ላይ ልዩ ነው ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን ተከትሎ፤ ማክሮን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መወያየታቸው የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ ማክሮን የተጓዙበት መንገድ ውጥረቱን ከማርገብ ይልቅ ጥረቶችን የሚጎዳ ነው በሚል ተተችተዋል፡፡
4 ሜትር ከሚረዝመው የፑቲንና ማክሮን የውይይት ጠረጴዛ ጀርባ ያለው ሚስጥር ምንድን ነው?
ፈረንሳይ ዩክሬንን በወታደራዊ እና በገንዘብ ስትደግፍ የቆየች ሀገር ብትሆንም ማክሮን እንደሌሎች የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ወደ ኪቭ በመጓዝ ለዩክሬን ያላቸውን ፖለቲካዊ ድጋፍ እና አጋርነት ሲገልጹ አልታዩም፡፡