ፑቲን የዩክሬንን ግዛቶች የጠቀለሉበትን ቀን አከበሩ
ምዕራባውያን ባለፈው አመት የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔም ይሁን ባለፈው ወር የተካሄደውን ምርጫ አይቀበሉትም
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ ወደ ግዛቷ እንዲጠቃለሉ ባደረገቻቸው ግዛቶች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የፈለጉትን መርጠውል ብለዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን የዩክሬንን ግዛቶች የጠቀለሉበትን ቀን አክብረዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ ወደ ግዛቷ እንዲጠቃለሉ ባደረገቻቸው ግዛቶች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የፈለጉትን መርጠውል ብለዋል።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን በግዛቶቹ ሩሲያ አካሄዱከት ያለችው ህዝብ ወሳኔዎች እውነተኛ አይደሉም የሚል ክስ ቢያቀርቡም ሩሲያ ግን አትቀበለውም።
የመጀመሪያውን ክብረበዓል በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ፑቲን የማጠቃለል ሂደቱ የተከናወነው አለምአቀፍ መርሆዎችን በመከተል ነው በማለት የውሳኔያቸውን ትክክለኛነት ይከላከላሉ።
ከዚህ በተጨማሪም የዶኔክስ፣ የሉሃንስክ፣ የዛፖሬዥያ እና የኬርሶን ነዋሪዎች ባለፈው ወር በተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ወደ ሩሲያ ለመካለል ያላቸውን ፍላጎት በድጋሚ አረጋግጠዋል ብለዋል።
ነገርግን ምዕራባውያን ባለፈው አመት የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔም ይሁን ባለፈው ወር የተካሄደውን ምርጫ አይቀበሉትም።
ምርጫዎቹ የተካሄዱት የሩሲያ ጦር ከፍተኛ ቁጥጥር በሚያደርግበት ወቅት ነበር። ሩሲያ አራቱንም ግዛቶች እስካሁን መሉበሙሉ መቆጣጠር አልቻለችም።
የግዛቶቹን መካተት የመጀመሪያ አመት ክብረበዓል በማስመልከት በሬድ አስኩየር ፑቲን ያልተሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት ተካሂዷል።
ሩሲያ ግዛቶቹን የያዘችው በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት ነበር።