ፑቲን ሩሲያ የቀጣዩን ትውልድ ሚሳይል መሞከሯን አስታወቁ
ፑቲን እንደዚህ አይነት መሳሪያ የሚተኮስብን ከሆነ ማንኛውም ጠላት መዳን እንዳይችል ተደርጎ ይመታል ሲሉ አስፈራርተዋል
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው እለት እንደተናገሩት ሩሲያ ከፍተኛ አቅም ያለው ስትራቴጂክ ሚሳይል በተሳካ ሁኔታ ሞክራለች
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ የቀጣዩን ትውልድ ሚሳይል መሞከሯን አስታውቀዋል።
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው እለት እንደተናገሩት ሩሲያ ከፍተኛ አቅም ያለው ስትራቴጂክ ሚሳይል በተሳካ ሁኔታ ሞክራለች።
ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ኑክሌር ሊሸከም የሚችል እና በሺዎች የሚቆጠር ማይል የሚምዘገዘግ ሚሳይል ሞክራለች ብለዋል ፑቲን።
ፕሬዝደንቱ በአመታዊው የጋዜጠኞች እና ተንታኞች ስብሰባ ላይ እንደገለጹት ሩሲያ ሌላኛው የቀጣይ ትውልድ ሚሳይል ቁልፍ አካል በሆነው የሳርማት ኢንተርናሽናል ሚሳይል ላይ የምታደርገውን ስራም አጠናቃለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያሉችን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረችበት ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ጀምሮ የሩሲያን የሚሳይል ኃያልነት የሚናገሩት ፑቲን ማገናዘብ የሚችል ማንም አካል በሩሲያ ላይ የኑክሌር ጥቃት አይሰነዝርም ብለዋል።
ፑቲን እንደዚህ አይነት መሳሪያ የሚተኮስብን ከሆነ ማንኛውም ጠላት መዳን እንዳይችል ተደርጎ ይመታል ሲሉ አስፈራርተዋል።
ሩሲያ ሶቬት ህብረት ለመፍረስ አንድ አመት እስከሚቀራት እስከ ፈረንጆቹ 1990 ድረስ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ሙከራ አላደረገችም። ነገርግን ፑቲን እንደዚህ አይነት ሙከራ የመጀመር እድል ስላለመኖሩ አልተናገሩም።
ሩሲያ የኑክሌር መኩራን የሚያግድ ስምምነት ብትፈርምም፣ አሜሪካ ግን ስምምነቱን አልፈረመችም ብለዋል ፑቲን።
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ዩኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ በሩሲያ፣ በአሜሪካ ወይም በሁለቱም የሚደመር ከሆነ በሁለቱ ሀገራት መካከል በ60 አመታት ውስጥ ከፍተኛ የተባለ ውጥረት ይፈጠራል።