በምእራባዊያን ሀገራት የሚነሱ ዜናዎች ሁሉ መሰረት የሌላቸው ተራ ፕሮፓጋንዳዎች መሆናቸውንም ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል
በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑን ፕሬዘንት ፑቲን ገለጹ፡፡
የሩሲያ ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸውን ለልዩ ተልዕኮ በሚል ወደ ዩክሬን ከላኩ ዛሬ ዘጠነኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በዚህ ዙሪያ መግለጫ የሰጡት ፕሬዘዳዳት ፑቲን በዩክሬን እያካሄዱት ያለው ጦርነት በታሰበበት እና በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
"በዩክሬን ያለው ጦራችን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተልዕኮውን በሚገባ እየፈጸመ ነው፣ በዩክሬን መስራት ያለብንን ስራዎች ሁሉ እያከናወኑ ነው" ብለዋዋ ፕሬዘዳንት ፑቲን፡፡
የምእራባዊያን አገራት በሩሲያ ጦር ላይ የሚነሱ ዜናዎች ሁሉ መሰረት የሌላቸው ተራ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው ያሉት ፕሬዘዳንቱ የዩክሬን ጦር ስደተኞች እና ንጹሃን ዜጎችን እንደ መያዣ እየተጠቀመ መሆኑንም አክለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በነበራቸው የስልክ ንግግር ሞስኮ ዩክሬን ውስጥ በምታካሂደው ዘመቻ ያቀደችውን ታሳካለች ብለዋል።
ፑቲን አስተዳደራቸው የኪዬቭን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማስቆም ለሩሲያ ደኅንት ወታደራዊ ስጋት እንዳትሆን እናደርጋለን ስለማለታቸው የሩሲያ መንግሥት አስታውቋል።
ሩሲያ የዩክሬንን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የማስቆም እና ገለልተኛ የማድረግ ዓላማ ማሳካት ትችላለች ሲሉ ቭላድሚር ፑቲን ለኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።
የሩሲያ እና የፈረንሳይ ፕሬዝደንቶች ለ90 ደቂቃዎች የዘለቀ የስልክ ንግግር ዛሬ ሐሙስ ማድረጋቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።
ከተጀመረ አንድ ሳምንት ባስቆጠረው ጦርነት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዩክሬናውያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል። የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ሁለተኛ ውይይታቸውን ጀምረዋል።