ሩሲያ በዩክሬን የከፈተችውን ጦርነት የሚቃወሙት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ሁሉ በመጣል ላየ ይገኛሉ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ እስካሁን 489 ወታደቿ እንደተገደሉባትና እና 1597 የሚሆኑት ደግሞ እንደቆሰሉባት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁን ሮይርስ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ በደረሰባት ጉዳት ላይ መግለጫ ስትሰጥ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ እንዳለው በሩሲያ ጥቃት ከ2870 በላይ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን እና 3700 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን ኢንተርፋክስ የተሰኘው የሩሲያ ሚዲያ ምንጭ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ነገርግን ዩክሬን ለአንድ ሳምንት ያህል በተካደው ጦርነት ከ5ሺ በላይ የሩሲያ ወታደሮች መገደላቸውን ገልጻለች፡፡
የሩሲያ እስካሁን ባካሄደችው ዘመቻ በደቡብዊ ዩክሬን የምትገኝው ኬርሶን ከተማ ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠር ችላለች፡፡ የሩሲያ ወታራዊ ዘመቻ በምእራበውያን ዘንድ ያልተወደደ በመሆኑ በርካታ የኢኮኖሚ ማእቀቦች ጎርፍ እየወረደባት ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው እለት ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡
የውሳኔ ሀሳቡ በ143 የድጋፍ ድምጽ፣35 ተአቅቦ እና በ5 ተቃውሞ ሩሲያ ከዩክሬን ለቃ እንድትወጣና ተኩስ እንድታቆም የሚያስጠነቅቀዉን የዉሳኔ ሀሳብ አጸድቋል።ቻይና እና ህንድ ድምጸ ተአቅቦ ካሰሙ ሀገራት ውስጥ ናቸው።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።
ከተጀመረ አንድ ሳምንት ባስቆጠረው ጦርነት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዩክሬናውያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል። የሩሳያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ውይይት ጀምረዋል።