ዩክሬን በክሬሚያ ያለውን የሩሲያ ጦር መርከብ በድሮን መምታቷን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘግበዋል
ሩሲያ እና ዩክሬን ከምርኮኞች ግድያ ጋር በተያያዘ እየተወነጃጀሉ ነው
በክሬሚያ ግዛት በምትገኘው ሴቫስቶፖል ከተማ ያለው የባህር ሃይል የድሮን ጥቃት ደርሶበታል
ዩክሬን በጥቁር ባህር ክሬሚያ የሚገኘውን የሩሲያ ጦር መርከብ በድሮን መምታቷ ተገለጸ።
በክሬሚያ ግዛት በምትገኘው ሴቫስቶፖል ከተማ ያለው የባህር ሃይል የድሮን ጥቃት እንደደረሰበት የሩሲያ ሚዲያዎችም እየዘገቡ ነው።
የግዛቲቱ አስተዳዳሪም ጥቃት ስለመድረሱ በቴሌግራም አስታውቀዋል ።ጥቃቱ የደረሰው ሩሲያ የባህር ኃይል ቀን እየተከበረ ባለበት ዕለት መሆኑም ተዘግቧል፡፡
የክሬሚያ ግዛት አስተዳዳሪ የባህር ኃይል ቀንን ለማክበር የተዘጋጀው መርሐ ግብር ለደህንነት ሲባል መሰረዙን አስታውቀዋል።
አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ባለስልጣን ዩክሬን በክሬሚያ ጥቃት መሰንዘሯን መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ዩክሬን ጥቃቱን የሰነዘረችው
የባህር ኃይል ቀንን ለማክበር ድግስ ሊደረግ በታሰበበት ወቅት መሆኑንም ባለስልጣኑ ተናግረዋል ተብሏል። ይህ የጥቃት ዜና የተሰማው ቭላድሚር ፑቲን ወደ ትውልድ ቀያቸው ሴንት ፔተርስበርግ ሄደው የባህር ኃይልን ቀን ለማክበር አስበው ሳለ መሆኑም ተገልጿል።
በክሬሚያ ግዛት በምትገኘውና የወደብ ከተማ በሆነችው ሴቫስቶፖል ከተማ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። የሩሲያው ሩሲያ ቱዴይ በጥቃቱ ስድስት ሰዎች መጎዳታቸውን ቢገልጽም ሮይተርስና አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ግን የተጎዱት አምስት ሰዎች ናቸው ብሏል።
ከቀናት በፊት ሩሲያ ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ በሆነ ሚሳየል በሩሲያ በሚደገፉት ተገንጣዮች ቁጥጥር ስር በሚገኝ ቦታ ታስረው የነበሩ 40 የሩሲያ የጦር ምርኮኞችን ገድላለች ስትል ክስ አቅርባለች፡፡ ነገርግን ዩክሬን ይህን ክስ አትቀበልም፡፡