ፕሬዝዳንት ፑቲን ምዕራባውያን በ1945 ሶቭየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀውን ድል ዘንግተውታል ብለዋል
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን ሀገራቸውን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው ብለዋል።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶቭየት ህብረትን የድል ቀን በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ፑቲን "እውነተኛ ጦርነት" በሩሲያ ላይ በድጋሚ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ፑቲን የሩስያ የድል በዓል አካል በሆነው በቀይ አደባባይ ሞስኮ የወደፊት ሰላምን ማየት እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
ሩሲያ በዩክሬን በሚካሄደው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" መላ ሀገሬው ሰው አብሮን ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፑቲን አክለውም በፈረንጆቹ 1945 ሶቭየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀውን ድል ምዕራባውያን ዘንግተውታል ብለዋል።