ፕሬዝደንት ፑቲን በሩሲያ ጦር እጅ ያለውን መሳሪያ እንደሚያዘምኑ ገለጹ
ፑቲን በሩሲያ ጦር እጅ ያሉት “የጦር መሳሪያዎች በቋሚነት እና በተከታታይነት” እንዲዘምኑ ይደረጋል ብለዋል ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ ጠቅልላለች
ፑቲን በሩሲያ ጦር እጅ ያሉት “የጦር መሳሪያዎች በቋሚነት እና በተከታታይነት” እንዲዘምኑ ይደረጋል ብለዋል
የሩሲያ ፕሬዝደንት ፑቲን አሁን በሩሲያ ጦር ጥቅም ላይ ያለውን መሳሪያ እንዲዘምን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ፑቲን በሩሲያ ጦር እጅ ያሉት “የጦር መሳሪያዎች በቋሚነት እና በተከታታይነት” እንዲዘምኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን የጦር መሳሪያዎችን ለማዘመን በጦር መሳሪያ አምራቾች ውድድር መኖር ያስፈልጋል ማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ዩክሬን ኔቶ ወደተሰኘው እና በአሜሪካ ወደሚመራው ወታደራዊ ጥምረት ትገባለች በሚል ስጋት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በርካታ ወራት ተቆጥረዋል፡፡
ሩሲያ ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት የሚያደርገው መስፋፋት ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት በመግጽ ነበር ጦርነት መክፈቷን ያስታወቀችው፡፡
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶች የግዛቷ አካል እንዲሆኑ በህዝበ ውሳኔ አስወስናለች፡፡
ፐሬዝደንት ፑቲን ወደ ሩሲያ በተጠቃለሉት ግዛቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ይቆጠራል ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት የሚያወግዙት ምእራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማእቀብ ከመጣል ባሻገር ዩክሬንን በጦር መሳሪያ እየረዱ ናቸው፡፡
aXA6IDMuMjEuOTMuNDQg ejasoft island