ፑቲን ኬርሰንና ዛፖሪዝያ ከዩክሬን ነፃ መሆናቸውን አወጁ
የሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ አዋጅ ኬርሰንና ዛፖሪዝያ ክልሎችን ወደ ሩሲያ ለማዋሃድ እየተወሰደ ያለ እርምጃ አካል ነው
ሩሲያ ኬርሰንና ዛፖሪዝያን ጨምሮ አራት የዩክሬን ክልሎችን ዛሬ በይፋ ወደ ግዛቷ ትቀላቅላለች
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኬርሰንና ዛፖሪዝያ ክልሎች ከዩክሬን በመነጠል ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ ፕሬዝዳንታዊ አዋጅ አወጁ።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኬርሰንና ዛፖሪዝያ ክልሎች ከዩክሬን ነፃ መሆናቸውን የሚገልጽ አዋጅ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸውም ተነግሯል።
አዲሱ የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ ሁለቱ ክልሎች ከዩክሬን ነጻ በመውጣታቸውን ማሳወቅ ሲሆን፤ ይህም ሁለቱን ክልሎች በመደበኛነት ወደ ሩሲያ ግዛት ከመዋሃዳቸው በፊት የተወሰደ እርምጃ ነው ተብሏል።
ሩሲያ በቁጥጥሯ ስር የሚገኙ አራት ዩክሬን ክልሎችን በዛሬው እለት በይፋ ወደ ግዛቷ ልትቀላቅል መሆኑን ክሬምሊን በትናትናቅ እለት አስታውቋል።
የክሬምሊን ቃለ አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በሰጡት መግለጫ፤ በዛሬው እለት በታላቁ ክሬምሊን ቤተ መንግስት አዳዲሶቹን የሩሲያ አካባዎች በይፍ የማዋሃድ የፊርማ ስነ ስርዓት ይካሄዳል ብለዋል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱም በዩክሬን ውስጥ የሚገኙት ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያ እና ኬህርሶን ክልሎች በይፋ የሩሲያ አካል እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በዩክሬን እንዲሁም በበርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ውግዘት የደረሰበት ህዝብ ውሳኔ ከመስከረም 13 ስከ መስከረም 17 ድረስ በሩሲያ በተያዙ ግዛቶች መካሄዱ ይታወሳል።
ህዝበ ውሳኔው የተካሄደው በአራት የዩክሬን ግዛቶች ላይ ሲሆን፤ ሉሃንስክ እና ዶኔትስክ ሪፐብሊኮች ያካተተ ነበር።
የህዝበ ውሳኔው ድምጽ አሰጣጥ መጠናቀቁን ተከትሎ በተካሄደው ቆጠራም 96 በመቶ ዩክሬናውያን ሩሲያን ለመቀላቀል መወሰናቸውን የሞስኮ ደጋፊ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
አራቱም የዩክሬን አካባቢዎች በህዝበ ውሳኔ ሩሲያን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባቸው ዩክሬን፤ የምዕራቡ ዓለም ትርጉም ያለው ወታደራዊ ድጋፍ ያድርግልኝ ስትል ተማጽናለች።
ሩሲያ በበኩሏ ሞስኮ፤ በሩሲያ ኃየሎች ስር የሚገኙትን የዶንባስ ግዛቶችን ለመከላከል ስትራቴጂካዊ የኒውክሌር ጦር ማሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል ማስጠንቀቋ ይታወሳል።