ፑቲን ሩሲያውያን ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ቁጥር እንዲጨምሩ አሳሰቡ
በ2023 መጀመሪያ ላይ የወጣው የመንግስት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ የሩሲያ ህዝብ ቁጥር ከ20 አመታት በፊት ከነበረው 149 ሚሊዮን ወደ 146.4 ሚሊዮን ዝቅ ብሏ
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለሀገሪቱ መቀጠል ሲባል ሩሲያውያን ቤተሰቦች ቢያንስ ሁለት ልጆችን መውለድ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል
ፑቲን ሩሲያውያን ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ቁጥር እንዲጨምሩ አሳሰቡ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለሀገሪቱ መቀጠል ሲባል ሩሲያውያን ቤተሰቦች ቢያንስ ሁለት ልጆችን መውለድ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።
ሩሲያ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ ቁጥሩን ይፋ ባታደረግም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ይነገራል። ከዚህ በተጨማሪም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን ጦርነቱን በመቃወም እና ለጦርነት እንመለመላለን በሚል ስጋት ሀገሪቱን ለቀው ወጥተዋል።
ፑቲን በኡራልስ ግዛት በሚገኘው የታንክ ፋብሪካ ለሚገኙ ሰራተኞች የሩሲያ ህዝብ ማንነቱን አስጠብቆ እንዲቀጥል ከተፈለገ አንድ ቤተሰብ ቢያንስ ሁለት ልጅ መውለድ ይገባዋል ሲሉ ነግረዋቸዋል።
ፑቲን "እንደ ሩሲያ እንደሚኖር ጎሳ(ብሔር) መቀጠል የምንፈልግ ከሆነ በቤተሰብ ቢያንስ ሁለት ልጆች መወለድ አለባቸው" ብለዋል።
"አንድ ቤተሰብ አንድ ልጅ ብቻ የሚኖረው ከሆነ የህዝብ ቁጥሩ ይቀንሳል። ስለዚህ ለማሰፋት እና ለማሳደግ፣ ቢያንስ ሶስት ልጆች ሊኖሯችሁ ይገባል።"
ፑቲን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ ቤተሰብ እና ሀገር የሚፈጥረው የባህላዊ የሩሲያ እሴቶች ደጋፊ ናቸው።
ፑቲን በ24 አመት የስልጣን ዘመናቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ጨምሮ በምዕራቡ አለም የሚቀነቀኑ ከዚህ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጥብቅ ክልከላ አስቀምጠዋል።
ሩሲያ ከሶቬት ህብረት መውደቅ በኋላ ባሉ ሁለት አስርት አመታት የህዝብ ቁጥሯ እየቀነሰባት ነው። በ2023 መጀመሪያ ላይ የወጣው የመንግስት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ የሩሲያ ህዝብ ቁጥር ከ20 አመታት በፊት ከነበረው 149 ሚሊዮን ወደ 146.4 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል።