አውሮፓ ራሱን መከላከል እንደማይችል ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ የዩክሬን ጦርነትን ለማሸነፍ ኑክሌር የጦር መሳሪያዎቿን መጠቀም አያስፈልጋትም ብለዋል
ሩሲያ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያ ማስታጠቃቸውን ካላቆሙ አውሮፓን እና አሜሪካንን መምታት ለሚፈልጉ አጋሮች ተመሳሳይ የጦር መሳሪያ ልናስታጥቅ እንችላለን ማለቷ ይታወሳል
አውሮፓ ራሱን መከላከል እንደማይችል ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናገሩ፡፡
የሩሲያዋ ፒተርስበርግ ከተማ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ጉባኤዋን አስተናግዳለች፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ፒተርስበርግ ከተማ ያመሩ ሲሆን ከጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠይቆችን አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ህጓን እንደማትቀይር እና ብሔራዊ ደህንነቷ አደጋ ውስጥ ሲገባ ብቻ እንደምትጠቀም ተናግረዋል፡፡
እንደ ፕሬዝዳንት ፑቲን ገለጻ ሩሲያ ከኑክሌር ጦር መሳሪያ ከመጠቀሟ በፊት ታክቲካል የኑክሌር ጦር መሳሪያ አላት ብለዋል፡፡
ሩሲያ አሜሪካንን ጨምሮ ከየትኛውም የዓለማችን ሀገራት በላይ ታክቲካል የኑክሌር ጦር መሳሪያ አላት ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ጦርነትን በበላይነት ለማጠናቀቅ ኑክሌር የጦር መሳሪያዎን መጠቀም አያስፈልጋትም ብለዋል፡፡
ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ
አውሮፓ እንደ ኑክሌር የጦር መሳሪያ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅም እንደሌለውም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
“አውሮፓ ራሱን ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አቅም እስከ ሌለው ድረስ ራሱን መከላከል የማይችል ነው“ ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዝዳንት ፑቲን ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያ መስጠታቸውን ካላቆሙ ሩሲያ አውሮፓን እና አሜሪካንን መምታት ለሚፈልጉ አጋሮቿ ልታስታጥቅ ትችላለች ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡