ሩሲያ “ብቻዋን አትቀርም፤አታፈገፍግምም” ሲሉ ፕሬዝደንት ፑቲን ምእራባውያንን አስጠነቀቁ
ሩሲያ የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን እና የሂውማን ራይትስ ዎች ቢሮዎችንም ዘግታለች
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ሁሉንም የምትፈልገውን አላማ ታሳካለች ብለዋል
በሶቬት ህብረት ጊዜ የነበረውን የስፔስ ስኬት በምሳሌነት የጠቀሱት የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን፤ ሩሲያን ለማግለል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም ሲሉ ምእራባውያንን አስጠንቅቀዋል፡፡
ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ የካቲት ወር በዩክሬን የጀመረችውን “ልዩ ወታራዊ ዘመቻ” ተከትሎ ማእቀብ ባዘነቡባት ምእራባውያን እና አሜሪካ ላይ እምነት እንደማይኖራትና ገልጻለች፡፡
በሶቬት ህብረት ጊዜ “ጠቅላላ ማእቀብ ተጥሎ ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ተገልላም ነበር፤ ነገርግን ሶቬት አሁንም በስፔስ ቀዳሚ ነች” ብለዋል ፑቲን በሩሲያ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእክት፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን የመገለል ፍላጎት እንደሌላቸው እና በዚህ ዘመናዊ አለም ማግለል እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሩሲያ በዩሪ ጋጋሪ አማካኝነት ወደ ስፔስ ያደረገችው በረራ እና በፈረንጆቹ 1957 የስፑትኒክ አንደኛ ወደ ስፔስ መብረር አሜሪካን አስደንግጦ ነበር፡፡ በወቅቱ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ለመወዳደር ስትል ናሳን አቋቁማ ነበር፡፡
ፑቱን በዩክሬን “ወታደራዊ ዘመቻ” ለማድረግ የተገደዱት፤ አሜሪካ ዩክሬንን እና ኔቶን በመጠቀም ለማስፈራራት ስለሞከረች እና ይህንም መከላከል ሲለሚገባ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ሁሉንም የምትፈልገውን አላማ ታሳካለች ብለዋል፡፡
በቅርቡ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄደው ስብሰባ ሩሲያን ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡ ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ ሩሲያ ያገደው የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን በሰብአዊ መብት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነበር፡፡
ይህን ውሳኔ ተከትሎ ሩሲያ ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አባልነት ወጥታለች፡፡
ሩሲያ የአምነስቲ እንተርናሽናል እና የሂውማን ራይትስ ዎች ቢሮዎችንም ዘግታለች፡፡