ሂውማን ራይትስ ዎች ያወጣው ሪፖርት ምክንያት ርምጃ እንዲወሰድበት ምክንያት መሆኑ ብዙም አያጠራጥም ብሏል
የሩሲያ የፍትህ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን እና ሂውማን ራይትስ ዎች ጨምሮ የ15 የውጭ ድርጅቶችን ፍቃድ በመንጠቅ ቢሯቸውን ዘግቷል፡፡
ሩሲያ የድርጅቶቹን ፍቃድ የሰረዘችበትን ዝርዝር ምክንያት አለማቅረቧን ሮይተር ዘግቧል፡፡
የሩሲያ ፍትህ ሚኒስቴር ይህን ወሳኔ ያሳለፈው ዋና መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ የተሳተፉ ወታደሮቿ የጦርንትን ህግ በመጣስ መጠና ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥስት አካሂደዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡
ምእራባውያ ሀገራት በሩሲያ ላይ የጦር ወንጅክ ፈጽማለች በማለት የሚያርጉትን ውንጀላ በተደጋጋሚ አስተባብላለች፡፡
ሂውማን ረይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት ምክንያት ርምጃ እንዲወሰድበት ምክንያት ስለመሆኑ ብዙም አያጠራጥም ብሏል፡፡
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ለማገድ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ኢትዮጵያ የተቃውሞ ድምጽ ሰጥታለች፡፡
193 አባልት ባሉት ጠቅላላ ጉባኤ፣በ93 ሀገራት ድጋፍ፣በ58 ድምጸ ተአቅቦ እና በ24 ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ለማገድ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ጽድቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ እግዱን የጣለው ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ወታደሮቿ መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ይህ ወሳኔ የተላለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ነው፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ግልጽ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን፤ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በሪፖርት ገልጿል።
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፣ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።
የዩክሬን ሃይሎች ጠንካራ ተቃውሟቸውን የፈጠሩ ሲሆን ምዕራባውያን ሩሲያ ኃይሏን እንድታስወጣ ከፍተኛ ማዕቀብ ጥለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ውይይታቸውን ጀምረዋል።