በመላው ፈረንሳይ የባቡር ትራንስፖርት ተቋረጠ
ትራንስፖርቱ የተቋረጠው ሆን ተብሎ በባቡር ሀዲዶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ነው ተብሏል
የፓሪስ ኦሎምፒክ ዛሬ ይጀመራል
በመላው ፈረንሳይ የባቡር ትራንስፖርት ተቋረጠ፡፡
በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው ተወዳጁ የኦሎምፒክ ውድድር ከ100 ዓመት በኋላ ወደ ፓሪስ ተመልሷል፡፡
ዛሬ አመሻሽ በሚጀመረው በዚህ ውድድር ላይ ከ7 ሺህ 500 በላይ የዓለም አትሌቶችን ጨምሮ ሚሊዮኖች ይታደሙታል፡፡
ይሁንና በመላው ፈረንሳይ ዛሬ አዳር በባቡር ሀዲዶች ላይ ሆን ተብሎ በተፈጸመ ጥቃት የባቡር ትራንስፖርት ተቋርጧል፡፡
የሀገሪቱ ባቡር ትራንስፖርት ድርጅት እንዳስታወቀው ሆን ተብሎ በባቡር ሀዲዶቹ ላይ በተፈጸመ ከባድ ጥቃት ምክንያት አገልግሎቱ መቋረጡን ገልጿል፡፡
ይህንን ተከትሎም በመላው ፈረንሳይ ፈጣን ባቡር ትራንስፖርት የተሰረዘ ሲሆን ጉዳዩ በሀገሪቱ ድንጋጤን ፈጥሯል ተብሏል፡፡
ጥቃቱ ዛሬ አመሻሽ በሚደረገው የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ውድድርን ለማስተጓጎል ታስቦ የተፈጸመ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ባለቤት ብሪጅት ማክሮን ጾታቸውን አስቀይረዋል ያሉ ጋዜጠኞች ላይ ክስ መሰረቱ
ለኦሎምፒክ ውድድር ወደ መክፈቻ ቦታው ለመጓዝ ቲኬት የገዙ ሰዎች ጉዟቸውን እንዲያራዝሙ ተጠይቀዋል፡፡
አደጋው በተለይም ፓሪስን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያስተሳስሩ የባቡር መሰረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል፡፡
የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስትር ፓትሪስ ቬርግሪት በኤክስ አካውንታቸው ለይ እንዳሉት ጥቃቱ የሀገሪቱ ባቡር ትራንስፖርትን ለቀጣዮቹ ቀናት ያስተጓጉላል ብለዋል፡፡
ጥቃቱን ያወገዙት ሚኒስትሩ የባቡር ትራንስፖርት ሰራተኞች የተቋረጠውን ትራንስፖርት ለመመለስ እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡