ትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል መግቢያ ውጤትን ይፋ አደረገ
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 31 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ ተፈታኞች ለሬሚዲያል ፕሮግራም ብቁ ናቸው ተብሏል
የሬሚዲያል ፕሮግራም ማለት ብሔራዊ ፈተቨና ተፈትነው ከ50 በመቶ በታች ላመጡ ተማሪዎች የሚሰጥ እድል ነው
ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 የሬሚዲያል መግቢያ ውጤትን ይፋ አደረገ፡፡
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ውሳኔን ፋ አድርጓል፡፡
የሬሚዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ውጤት መቀነስ በትምህርት ዘርፉ እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲሁም ተዛማጅ ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘረጋ አሰራር መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት የ2017 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያላቸዉን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሬሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን አስታውቋል።
የተየፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 የተፈተኑት 204 እና ከዛ በላይ ማምጣት እንዲሁም ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 600 እና ከዛ በላይ 192 ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
የታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 የተፈተኑ ከሆነ 192 እና ከዛ በላይ ማምጣት ሲጠበቅባቸው ሴቶች ደግሞ ከ600ው 186 እና ከዛ በላይ ማምጣት አለባቸው ተብሏል፡፡
ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች ከ500ው 160 እና ከዛ በላይ፣ እንዲሁም ሴቶች ደግሞ 155 እና ከዛ በላይ ሆኖ ተቆርጧል፡፡
በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተየፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700ው 238 እና ከዛ በላይ በተመሳሳይ በሴቶች ደግሞ 224 እና ከዛ በላይ ማምጣት አለባቸው ተብሏል፡፡