ሱዳን ኦማር አልበሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከተወገዱ በኃላ ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ ገብታለች
የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል(አርኤስኤፍ) ለሰብአዊነት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከዛሬ ጠዋት 2 ሰአት ደምሮ ለ72 ሰአታት ተኩስ ለማቆም መስማማቱን አስታውቋል።
ተኩስ አቁም ከኢድ አልፈጥር በዓል ጋር ተገጣጥሟል።
ዛሬ ጠዋት ካርቱም በቦምብ እና በተኩስ ተናወጣለች።
የሱዳን ጦር በዚህ ጉዳይ ፈጣን ምላሽ አልሰጠም፤ዋና አዛዡ ጀነራል አብደልፈታህ አል-ቡርሃንም በሰራዊቱ የፌስቡክ ገፅ ላይ በተለጠፈው እና ቀድሞ በተቀረጸው ንግግር ላይ ስለተኩስ አቁም ስምምነትን አላነሱም።
አርኤስኤፍ በመግለጫው "እርቁ ከተከበረው የኢድ አልፈጥር በዓል ጋር የተገጣጠመ ነው ... ዜጎችን ከግጭት ቀጠና እንዲርቁ እና የሰብአዊነት ኮሪደሮችን ለመክፈት እና ለቤተሰቦቻቸው ሰላምታ እንዲሰጡ እድል ለመስጠት" ብሏል።
ባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአርኤስኤፍ እና በሱዳን ጦር መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት ሀገሪቱን ወደ ሲቪል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር የተያዘውን እቅድ አደጋ ላይ ጥሎታል።
ሱዳን የእስላማዊው ገዢ ኦማር አልበሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከተወገዱ በኃላ ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
አርኤስኤፍ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሲል የገለጸውን ጥቃት ለመመከት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ገልጿል።
ኤርኤስእፍ “የተሟላ የተኩስ አቁም” ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሯል።
ቀደም ሲል አጋር በነበሩት ሁለት የገዢው ወታደራዊ ጁንታ መሪዎች፣የጦር ኃይሎች አዛዥ ቡርሃን እና የአርኤስኤፍ መሪ ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ መካከል በተደረገው የስልጣን ሽኩቻ ቢያንስ 350 ሰዎች ተገድለዋል።
ግጭቱ በሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የመሻሻል ተስፋን አጨልሟል፣ ጎረቤቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል እና በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል በሚደረገው አህጉራዊ ውድድር ውስጥ ሊገባ ይችላል።
አርኤስኤፍ ቀደም ሲል አዲስ ጥቃት ነው ያለውን አውግዟል።
"በአሁኑ ሰአት ዜጎች የመጀመሪያውን የኢድ አልፈጥርን በዓል ለመቀበል በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት የካርቱም ሰፈሮች በአይሮፕላኖች እና በከባድ መሳሪያዎች ላይ የቦምብ ጥቃቶችን እያነቁ በመኖሪያ ሰፈሮች ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈጸሙ ነው" ሲል አርኤስኤፍ ከሷል።
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሐሙስ ዕለት ሲቪሎች ወደ ደኅንነት እንዲደርሱ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል።
ሐሙስ ዕለት የተኩስ እና የፍንዳታ ድምፅ ሲሰማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ከካርቱም ወጥተዋል።
በምዕራባዊው የዳርፉር ግዛት የሚካሄደውን ጦርነት ለመሸሽ ወደ ቻድ አቋርጠዋል።
የሃኪሞች ቡድን ሃሙስ ዕለት ከካርቱም በስተ ምዕራብ በምትገኝ ኤል-ኦቤይድ ከተማ ቢያንስ 26 ሰዎች ሲገደሉ 33 ቆስለዋል ብሏል።
በጦር ኃይሉ እና በአርኤስኤፍ ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩን እና ከፍተኛ ዘረፋ መፈጸሙን በቦታው የነበሩ እማኞች ገልጸዋል።