ሩሲያ የቦይንግ እና ኤርባስ ምርቶችን ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንደምታቆም አስታወቀች
ሩሲያ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ጋር ያላት ግንኙነት ላይጠገን መበላሸቱን አስታውቃለች
ሞስኮ በቀጣዮቹ ሰባት ዓመታ ውስጥ አንድ ሺህ አውሮፓላኖችን ለማምረት ማቀዷን ገልጻለች
ሩሲያ የቦይንግ እና ኤርባስ ምርቶችን ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንደምታቆም አስታወቀች።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ በሚል ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት መግባቷን ተከትሎ ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦች በሞስኮ ላይ ተጥለዋል።
ማዕቀቦቹን ተከትሎ ሩሲያ በሁሉም መንገድ ራሷን ለመቻል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ስትሆን ከአውሮፓ እና አሜሪካ ጋር የነበራትን የንግድ እንቅስቃሴ በማቋረጥ ላይ ተገ ኛለች ተብሏል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ሩሲያ ሙሉ ለሙሉ የቦይንግ እና ኤርባስ ምርቶችን ላለመጠቀም የወሰነች ሲሆን፤ እስከ 2030 ባሉት ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በሩሲያ የተሰሩ 1 ሺህ አውሮፓላኖችን ለማምረት አቅዳለች።
የሩሲያ መንግስታዊ የአቪዬሽን ተቋም ሮስቴክ እንዳለው ከሆነ ከአሜሪካ እና ምዕራባዊያን ጋር ያለው ግንኙነት በዘላቂነት መበላሸቱን ተከትሎ ወታደራዊም ሆነ የሲቪል አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖችን በሀገር ውስጥ ለማምረት መወሰኑን አስታውቋል።
በሩሲያ ለሲቪል አገልግሎት እየሰጡ ካሉ አውሮፓላኖች ውስጥ 95 በመቶዎቹ የቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያ ምርቶች ሲሆኑ በሞስኮ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች ሙሉ ለሙሉ ከዚህ በፊት ከኩባንያዎቹ ጋር የነበሩ ስምምነቶችን እንዲቆሙ ያስገድዳሉ ተብሏል።
የሮስቴክ ሀላፊ ለሮይተርስ እንዳሉት የቦይንግ እና ኤርባስ ምርቶች ከእንግዲህ በሩሲያ ምድር አይገጣጠሙም፣ ሞስኮ ከማንኛውም ሀገር ጥገኝተት የተላቀቀ አቪዬሽን ተቋም ትገነባለች ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንጆቹ ከ2007 ዓመት ጀምሮ ሮስቴክ የተሰኘ መንግስታዊ የአቪዬሽን ተቋም እንዲመሰረት ያደረጉ ሲሆን ይህ ተቋም የሀገሪቱን ወታደራዊ የጦር አውሮፕላኖችን ሲያመርት ቆይቷል።
ተቋሙ በወታደራዊ አውሮፓላኖች ማምረት ያገኘውን ልምድ ወደ ሲቪል አውሮፕላን ማምረት እንደሚሸጋገር የተገለጸ ቢሆንም ሩሲያ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ አንድ ሺህ አውሮፕላን ማምረት ሊከብዳት ይችላል የሚሉ ተቋሙ በወታደራዊ አውሮፓላኖች ማምረት ያገኘውን ልምድ ወደ ሲቪል አውሮፕላን ማምረት እንደሚሸጋገር የተገለጸ ቢሆንም ሩሲያ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ አንድ ሺህ አውሮፕላን ማምረት ሊከብዳት ይችላል የሚሉ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው።