የሩሲያ አየር መከላከያ በሞስኮ አቅራቢያ ጥቃት ልታደርስ የነበረች ድሮን መትቶ መጣሉን የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶብያኒን ተናግረዋል
በሩሲያ ዋና ከተማ አቅራቢያ ተቃጣው ጥቃት መክሸፉን የሞስኮ ከንቲባ ተናገሩ።
የሩሲያ አየር መከላከያ በሞስኮ አቅራቢያ ጥቃት ልታደርስ የነበረች ድሮን መትቶ መጣሉን የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶብያኒን ተናግረዋል።
ሁለቱ የሞስኮ አየር መንገዶች-ቩኮቮ እና ዶሞዴዶቮ የድሮን ጥቃት ሲከሰት ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት በረራ አቁመው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
ሶስተኛው አየርመንገድ ዙኮቭስኪም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ ነበር።
ከሞስኮ ከተማ በደቡብ ምዕራብ የሚገኘው የካሉጋ አየር መንገድም በረራ እንዲቆም እና አውሮፕላኖች እንዳያሮፍ አግዶ መቆየቱ ተገልጿል።
ሩሲያ እንዲህ አይነት ጥቃቶች በመፈጸም ዩክሬንን ተጠያቂ ስታደርግ ቆይታለች። ነገርግን ዩክሬን በሩሲያ ድንበር ውስጥ በሚፈጸሙ ጥቃቶት ላይ ብዙም አስተያየት አትሰጥም።
ከዚህ በፊት በሩሲያ ቤተመንግስት ክሬሚሊን ላይ ጥቃት ሊያደርስ የነበረ ድሮን ተመትቶ መውደቁ ይታወሳል። በድሮን ጥቃቱ ፕሬዝደንት ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ ያለመ ነበር በሚል መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
በወቅቱ ጥቃቱ የዩክሬን የሽብር ድርጊት ነው ያለችው ሩሲያ የአጸፋ መልስ እንደምትሰጥ ዛቻ አሰምታለች።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 21 ወራት አልፎታል።