የሩሲያ ጦር ቁልፍ ተብላ በምትጠራው ፖክሮቭስክ ከተማን እየከበበ ነው ተባለ
ፖክሮቭስክ ከተማ የዩክሬን ጦር ቁልፍ የሎጅስቲክስ ማዕከል ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች
ዩክሬን የሩሲያን ጦር ለመግፋት ከሌሎች የውጊያ ድንበሮች ሳይቀር ወታደሮቿን በማስፈር ላይ ናት ተብሏል
የሩሲያ ጦር ቁልፍ ተብላ በምትጠራው ፖክሮቭስክ ከተማን እየከበበ ነው ተባለ።
አንድ ሺህ ቀን ያለፈው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እንደቀጠለ ሲሆን አዳዲስ ክስተቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ዩክሬን ባሳለፍነው ነሀሴ በምስራቅ የውጊያ ግምባር የሩሲያን ጦር ግስጋሴ ለመግታት በሚል በኩርስክ በኩል አዲስ ጥቃት ከፍታ ነበር።
ዩክሬን ሩሲያን በኩርስክ በኩል ውጊያ ማጥቃት የጀመረችው ፖክሮቭስክን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ ያለው የሩሲያ ጦር ለመግታት ነበር።
ይሁንና ሩሲያ ፖክሮቭስክ ከተማን ለመቆጣጠር የጀመረችውን ውጊያ ከማቋረጥ ይልቅ የቀጠለች ሲሆን ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ጫፍ ላይ ደርሳለች ተብሏል።
ዩሮ ኒውስ የብሪታንያ መከላከያ ያወጣው መግለጫን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የሩሲያ ጦር ፖክሮቭስክ ከተማን ለመቆጣጠር አንድ ሶስት ኪሎ ሜትር ብቻ ቀርቶታል ብሏል።
ከተማዋ የዩክሬን ጦር ቁልፍ የሎጅስቲክስ እና ወታደራዊ አመራር መስጫ ማዕከል ሆና ስታገለግል ቆይታለች።
ይህ በዚህ እንዳለ ዩክሬን ከተማዋን ላለመነጠቅ ስትል በሌሎች ግምባሮች ያሉ ወታደሮቿን በማንሳት ወደ ምስራቅ ግምባር እያሰፈረች እንደሆነ ተገልጿል።
ፖክሮቭስክ ከተማ አንድ ሚሊዮን ገደማ ነዋሪዎች ይኖሩባታል ከምትባለው ድንፒሮ ከተማ የ20 ኪሎ ሜትር ርቀት አላት።
ሩሲያ ይህችን ከተማ ከተቆጣጠረች ጦርነቱ ወደ መካከለኛው ዩክሬን ይገባልም ተብሏል።
ሩሲያ ሙሉ ለሙሉ የዶንቴስክ ግዛትን ለመቆጣጠር ፍላጎት አላት የተባለ ሲሆን አሁን ላይ 60 በመቶ አካባቢዎችን መቆጣጠሯም ተገልጿል።