በየመን የተፈጸመውን ድብደባ ተከትሎ ሩሲያ የጸጥታው ም/ቤት እንዲሰበሰብ ጠየቀች
ሁለቱ ሀገራት ጥቃቱን ያደረሱት የሀውቲ አማጺያ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው
አሜሪካ እና ዩኬ በየመን ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ሩሲያ የተመድ የጸጥታው ምክርቤት እንዲሰብሰብ ጠይቃለች
አሜሪካ እና ዩኬ የመንን መደብደባቸውን ተከትሎ ሩሲያ የጸጥታው ም/ቤት እንዲሰበሰብ ጠየቀች።
አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም(ዩኬ) በየመን ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ሩሲያ የተመድ የጸጥታው ምክርቤት እንዲሰብሰብ ጠይቃለች።
ሩሲያ ስብሰባውን የጠራችው አሜሪካ እና ዩኬ በየመን ስላደረሱት የአየር ድብደባ ውይይት ለማድረግ መሆኑን ሮይተረሰ ዘግቧል።
በተመድ የሩሲያ ቋሚ ልኡክ የጸጥታው ምክርቤት በጥር 12 አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርቧል።
አሜሪካ እና ዩኬ ከአየር እና ከባህር በሀዉቲ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሁለቱ ሀገራት ጥቃቱን ያደረሱት የሀውቲ አማጺያ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ነው።
ከእስራኤል ጋር ጦርነት እያካሄደ ላለው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ድጋፍ እንደሚያደርግ የሚገልጸው የሀውቲ አማጺ ቡድን፣ ወደ እስራኤል በሚያቀኑ መርከቦች ላይ ጥቃት እሰነዝራለሁ ሲል ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካ በቀይ ባህር ላይ ያለውን የመርከቦች እንቅስቃሴ ሰላማዊ ለማድረግ በርካታ ሀገራት የተሳለፉበት ግበረ ኃይል አቋቁማለች።
የየመኑ ሀውሂ ቃል አቀባይ አሜሪካ እና ዩኬ ጥቃት ለማድረስ ምንም አሳሚኝ ምክንያት የላቸውም ብሏል።
ቃል አቀባዩ አክሎም ወደ እስራኤል በሚያቀኑ መርከቦች ላይ የሚደረገው ጥቃት እንደሚቀጥል ገልጿል።
በቀይ ባህር ላይ ያለው ግጭት፣ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ቀጠናዊ እየሆነ የሚለውን ስጋት ተጨባጭ የሚያደርግ ነው ተብሏል።