የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘውን ሮዝዶሊቪካን መቆጣጠሩን ገለጸ
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን የጀመረችው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው
ሩሲያ ከወራት በፊት በምስራቅ ዩክሬን በዶኔስክ ግዛት ወሳኝ የተባለችውን አቭዲቪካ ከተማን እና በርካታ መንደሮችን መቆጣጠር መቻሏ ይታወሳል
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘውን ሮዝዶሊቪካን መቆጣጠሩን ገለጸ።
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘውን የሮዝዶሊቪካ መንደርን መቆጣጠሩን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በደቡብ በኩል የተሰማራው የሩሲያ ጦር ቡድን የዩክሬንን ኃይሎች በዶኔስክ ግዛት ከምትገኘው መንደር ካስለቀቀ በኋላ ምቹ የሆነ ቦታ ይዟል ብሏል።
ሮይተርስ ሩሲያ አገኘሁት ያለችውን ድል ማረጋገጥ እንዳልቻለ ጠቅሷል።
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን የጀመረችው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
ሩሲያ ከወራት በፊት በምስራቅ ዩክሬን በዶኔስክ ግዛት ወሳኝ የተባለችውን አቭዲቪካ ከተማን እና በርካታ መንደሮችን መቆጣጠር መቻሏ ይታወሳል።
ዩክሬን እነዚህን ቦታዎች ለቃ የወጣችው የምዕራባውያን ወታደራዊ እርዳታዎች በወቅቱ ባለመድረሳቸው ነው የሚል ምክንያት ሰጥታ ነበር።
ሩሲያ፣ ዩክሬን በተከታታይ የከባድ መሳሪያ እና የድሮን ጥቃት የምትሰነዝርባትን በድንበር አካባቢ የምትገኘውን ቤልጎሮድን ለመከላከል በዩክሬኗ ካርኪቭ ግዛት በቅርቡ ያልተጠበቀ ጥቃት ፈጽማለች።
በዚህ ጥቃት ሩሲያ በካርኪብ ግዛት ያሉ በርካታ መንደሮችን ተቆጣጥራለች።
ይህን ተከትሎ ምዕራባውያን ሀገራት ዩክሬን በለገሷት መሳሪያዎች ሩሲያ ውስጥ ያለ ኢላማ እንድትመታ ፈቅደውላታል። ሩሲያ ይህን የምዕራባውያንን ውሳኔ "በእሳት መጫወት" ነው ስትል መግለጿ ይታወሳል።