ሩሲያ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የወንጀል ክስ መሰረተች
የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዳኞች በፕሬዝዳንት ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ አውጥተዋል
ሞስኮ ፑቲን የወንጀል ተጠያቂ የሚያደርጋቸው መሰረት የለም ብላለች
የሩሲያ መርማሪ ኮሚቴ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የጦር ወንጀል የእስር ማዘዣ ባወጡት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ እና ዳኞች ላይ የወንጀል ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
ከባድ ወንጀሎችን የማጣራት ኃላፊነት የተጣለበት ኮሚቴው፤ በፑቲን በኩል ምንም የወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ መሰረት እንደሌለ ገልጿል።
- የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ
- የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን የምእራባውያን ዋና አላማ "ሩሲያን መበታተን ነው” አሉ
የሀገራት ርዕሰ መስተዳድሮች በውጪ ሀገራት ያለመከሰስ ፍጹም መብት አላቸውም ብሏል።
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ የወሰደው እርምጃ በሩሲያ ህግ መሰረት ወንጀል የሚያሰኝ ምልክቶችን ያሳያል ሲል ኮሚቴው ገልጿል።
ይህም ወንጀል "ንጹህ ሰውን" በወንጀል መክሰስ እና "ዓለም አቀፍ ግንኙነትን ለማወሳሰብ የውጭ ሀገር ተወካይ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን" ኮሚቴው ተናግሯል።
የሩስያ እርምጃ አርብ እለት በፑቲን ላይ ለቀረበ የፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ምላሽ የመስጠት ተምሳሌታዊ ምልክት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፑቲን እና የሩሲያ የህጻናት ኮሚሽነር ከዩክሬን ወደ ሩሲያ ህጻናትን በማፈናቀል በጦር ወንጀል ተከሰዋል።
ክሬምሊን እርምጃውን "የማይገባ" ያለችው ሲሆን፤ ህጋዊ ተፈጻሚነቱም ባዶ ነው ብላለች። ሩሲያ የአይሲሲ ስምምነት ፈራሚ ሀገር አይደለችም።