ሩሲያ የዩክሬን ደህንነት ሀላፊ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች
የዩክሬን ደህንነት ሃለፊ ቫሲል ማሉይክ ከአንድ ሳምንት በፊት በሞስኮው የደረሱ የሽብር ጥቃቶችን አቀነባብረዋል በሚል ተከሰዋል
ዩክሬን በበኩሏ ከሩሲያ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች
ሩሲያ የዩክሬን ደህንነት ሀላፊ ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች፡፡
ከአንድ ሳምንት በፊት በሩሲያ መዲና ሞስኮ ባለ የሙዚቃ አዳራሽ ውስጥ በተፈጸመ የሽብር ድርጊት 144 ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በለቀይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡
ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ አምስት ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን የሩሲያ ደህንነት ባለስልጣናት ከጥቃቱ ጀርባ ዩክሬንን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትን ይፋ አድርገዋል፡፡
ከሞስኮው የሽብር ጥቃት ጀርባ የዩክሬን ደህንነት ሃለፊ እጃቸው አለበት የምትለው ሩሲያ የኪቭ ደህንነት ሃለፊ ቫሲል ማሉይክ ተላልፈው እንዲሰጧት በይፋ መጠየቋን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ አክላም የዩክሬን ደህንነት ሃለፊ ከሞስኮው በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ በተካሄዱ የሽብር ጥቃቶች ላይ ተሳትፎ እንዳላቸውም ገልጻለች፡፡
በተለይም የክሪሚያ ድልድይ ጥቃት፣ ታዋቂ ሰዎች እና ወታደራዊ ተንታኝ ጋዜጠኞች እንዲገደሉ የኪቭ ደህንነት ሃለፊ ቫሲል ማሉይክ ማቀነባበራቸውን ሩሲያ አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ ከዩክሬን ባሻገር በሌሎች ሀገራት ጦርነት ለመክፈት አስባለች?
ዩክሬን በበኩሏ የሩሲያን ጥያቄ ውድቅ ያደረገች ሲሆን ፕሬዝዳንት ፑቲን እና አስተዳድራቸው ሽብርተኛ ነው ስትል ገልጻለች፡፡
የዩክሬን ደህንነት ባወጣው መግለጫ ሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ዩክሬናዊን ህጻናትን ከወላጆቻቸው በማለያየት እና ሌሎች ወንጀሎች ተፈላጊ ወንጀለኛ መሆናቸውን አትርሱት ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በሞስኮ በደረሰው የሽብር ጥቃት በአፍጋኒስታን እንደሚንቀሳቀስ የሚገለጸው የአይኤስ ሽብር ቡድን ሀላፊነት እወስዳለሁ ቢልም ሩሲያ ግን ጥቃቱ በዩክሬን አቀነባባሪነት የደረሰ እንጂ በአይኤስ አይደልም ብላለች፡፡