ፖለቲካ
ሩሲያ ዩክሬን ሞስኮ ከተማ ላይ ልትፈጽም የነበረን ጥቃት አከሸፍኩ አለች
የሩሲያ አየር ሃይል ሁለት የዩክሬን ድሮኖችን በአየር ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል
ዩክሬን በሩሲያ ስለቀረበባት ክስ እስካሁን ያለችው ነገር የለም
ዩክሬን በሞስኮ ከተማ ላይ በድሮን ልትፈጽም የነበረ ጥቃት ማክሸፉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዩክሬን የሩሲያ መዲና በሆነችው ሞስኮ ላይ የሽብር ጥቃት ሰንዝራለች ሲል ከሷል።
የዩክሬን ድሮኖች በሞስኮ ላህ ጥቃት ለመሰንዘር ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ላይ የሞስከለን አየር ክልል ጥሰው እንደገቡም ታውቋል።
ይሁን እንጂ የሩሲያ አየር ሃይል በወሰደው እርምጃ ሁለቱም ድሮኖች በአየር ላይ እንዳሉ መትቶ መጣሉን እና በሞስኮ ላይ የሀቃጣውን ጥቃት ማክሸፉን አስታውቋል።
ከሁለቱ ድሮኖች አንደኛው በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ የወደቀ ሲሆን፣ ምንም ጉዳት እንዳላደረሰም ነው የተገለጸው።
ሁለተኛው ድሮን በማእከላዊ ሞስኮ በሚገኝ የንግድ ህንጻ ላይ መውደቁን እና የህንጻው የተወሰኑ ክፍሎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱም ተነግሯል።
የዛሬው ጥቃት የመጣው ዩክሬን ሩሲያ በጥቁር ባህር ወደብ በሆነችው ኦዴሳ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት አጸፋ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ ነው።
ሆኖም ግን ዩክሬን በሞስኮ ላይ ተሚክሮ ከቨፈ ስለተባለው የድሮን ጥቃት ክስ እስላሁን ምላሽ አልሰጠችም።