ሩሲያ ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከተደረገው ስምምነት ራሷን አገለለች
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የሩስያን እርምጃ ቀድሞውን የሚጠበቅ ነው ብለዋል
ሩሲያ ዩክሬን በጥቁር ባህር በሴቫስቶፖል መርከብ የድሮን ጥቃት ፈጽማለች በሚል ከሳለች
ሩሲያ ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከተደረገው ስምምነት ራሷን ማግለሏን አስታወቀች።
በፈረንጆቹ ሀምሌ 22 2022 በተመድ አመካኝነት ዩክሬን በጥቁር ባህር እህል ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንድታደርግ በሩሲያ፣ ቱርክ እና ዩክሬን መካከል መደረሱ ይታወሳል።
ለ120 ቀናት የሚቆየውን ስምምነት ተከትሎ ዩክሬን በየካቲት 24 ቀን ሩሲያ ጎረቤቷን በወረረችበት ጊዜ የቆመውን የጥቁር ባህር እህል እና የማዳበሪያ ኤክስፖርት እንደገና መጀመር ችላ ነበር።
ሆኖም ግን ሩሲያ ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ ከተደረገው ስምምነት ራሷን ማግለሏን ይፋ አድርጋለች።
ሩሲያ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ዩክሬን በጥቁር ባህር ላይ በነበረች በሴቫስቶፖል መርከብ ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት አድርሳለች በሚል ነው።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በቅዳሜው ጥቃት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በእህል ስምምነት ላይ በተሳተፉ መርከቦች ላይ ያነጣጠረ ነው፤ በዚህም አንድ መርከብ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጿል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የሩስያ ውሳኔ ዛሬ የተደረገ ሳይሆን በመስከረም ወር "የምግብ ምርታችንን የመርከቦችን እንቅስቃሴ የዘጋች" ጊዜ የመጣ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የዓለም ሀገራት ለሩሲያ እርጃ ጠንካራ አለምአቀፍ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
በስምምነቱ ቀደም ሲል ከ9 ሚሊዮን ቶን በላይ እህል ከዩክሬንወደ ውጭ ለመላክ መቻሉ ተነግሯል።
ዩክሬን ከጥቁር ባህር ወደቦች እህል ወደ ውጭ እንድትልክ የተደረገው ስምምነት በፈረንጆቹ የፊታችን ህዳር 19 እንደገና መታደስ ነበረበት።
ተመድ በትናንትናው እለት እንዳሰሰበው በተመድ አመካኝነት ዩክሬን በጥቁር ባህር እህል ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንድታደርግ የሚያስችለው ስምምነት እንዲራዘም ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡